ፊደል ፖስት ከታማኝ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት በቦሌ ቡልቡላ እና በቦሌ በሻሌ 8,000 ቤቶች አዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ከሶስት ወር ገደማ በፊት እጣ እንዲወጣባቸው ዝርዝር መረጃ ቢሰጥም ቤቶቹ እጣ እንዳልወጣባቸው መገንዘብ ችሏል ።
ቤቶቹ ባለፈው ክረምት ላይ እጣ ይወጣባቸዋል ተብሎ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በአስተዳደራዊ ስራ መጓተት ምክንያት ቤቶቹ እጣ እንዳልወጣባቸው ምንጮች የገለፁ ሲሆን አዲሷ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ምን አልባት በቅርብ ወራት ውስጥ እጣ እንዲወጣ ያደርጉባቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገልፀዋል።
በ40/60 ኮንዶሚንየም ቤቶች የተመዘገበው ሰው ቁጥር 100,000 ቢደርስም በሰባት አመት ውስጥ በሁለት ዙር የተላለፉት ቤቶች ቆጥር ከ20,000 አይበልጥም።
ለቤቶቹ ግንባታ መዘግየት ከእቃ አቅርቦትና ችግር ጋር ተያይዞ ደካማ የግንባታ ሂደት እንደዋነኛ ምክንያት ይጠቀሳል።