ከኮሮና ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ የላም ወተት ግዢ በግማሽ እንደቀነሰ ጥናት አመለከተ



ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩትእና ዓለም አቀፍ የምግብ ፖሊሲ ምርምር ኢንስቲትዩት የተባሉ ተቋሞች በጥናት አገኘሁት አንዳሉት በአዲስ አበባ የጥሬ ላም ወተት ግዢ ፍላጎት ኮሮናቫይረስ በሀገሪቱ ከተከሰተ በኋላ 50 ከመቶ መቀነሱን ጠቁመዋል።

ጥናቱ ገዢዎች ጥሬ ላም ወተትን መግዛትን ለምን ከኮሮናቫይረስ መጋለጥ ጋር እንዳያያዙት የገለፀው ነገር የለም።

ጥናቱ የፓሰቸራይዝድና የዱቄት ወተት ግዢ ፍላጎት ከወትሮ በተለየ በአዲሰ አበበ መጨምሩን አመላክቷል።

በተመሳሳይ በገጠሯም የኢትዮጵያ ክፍሎች የላም ወተት ግዢ ፍላጎት በ11 ከመቶ አንደቀነሰ የተነገረ ሲሆን በዚህ ምክንያት በሀገሪቱ ጥሬ የላም ወተት በመሸጥ በማከፋፈል የሚሰሩ ሰዎችን ገቢያቸው ላይ ከባድ ተፅእኖ አድሯባቸዋል።

ቫይረሱ ከተከሰተ በኋላ የአይብ ዋጋም ሀገሪቱ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን አስከ 40 ከመቶ ጨምሮ የነበረው የእንሰሳት መኖ ዋጋም ወደ ታች መውረዱን ጥናቱ ያስረዳል።
የእንሰሳት መድሀኒት ዋጋ ግን አስከ 20 ከመቶ ድረስ መጨመሩ ተጠቅሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *