ዳናይት ከቃና ቴሌቭዥን ተባራለች ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን ጣቢያው አስታወቀ



በቃና ቴሌቭዥን ‘ሀሽ ታግ ‘ፕሮግራም ላይ በአቅራቢነት የምትታወቀው ወላንሳ መክብብ( ዳናይት) ሰሞኑን ከኢንስታግራም ላይ ተወስዶ ሺሻ ከሚያጨስ ወጣት ጋር ተቀምጣ የሚያሳየውና በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች የተለቀቀው ቪድዮዋ ተከትሎ ከቃና ቴሌቭዥን ተባራለች ተብሎ በአንዳንድ ፌስቡክና ፣ቴሌግራም እና ዌብሳይቶች የተለቀቀው ዜና ” ሀሰት ነው ሲል ” ጣቢያው ለፊደል ፖስት ገልፇል።
ቃና ቪዲዮውን ተከትሎ ዳናዊት አባሯቷል ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የጣቢያው ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ሀይሉ ተክለሃይማኖት ” አልተባረረችም ከዚህ በላይ ግን የምሰጠው አስተያየት የለኝም ” ሲሉ መልሰዋል።
በተለቀቀው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተሰጠ አስተያየቶች መሀል “ግለሰባዊ መብቷ ነው ” ያሉ ሰዎች ሲኖሩ አንዳንዶቹ ደግሞ” ብዙ ሰው የሚከተላት ሴት በእንዲህ ያለ ቦታ ሆና የሚያሳይ ቪዲዮ ባይለቀቅ መልካም ነበር “ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *