ቻድ ከአንጎላ የወሰደችውን ብድር በገንዘብ መክፈል ስላቃታት ቁም ከብት በመላክ አየከፈለች ነው



ቻድ ከአንጎላ የወሰደችውን 100 ሚልየን ዶላር ብድር በገንዘብ መክፈል ስላልቻለች በጀልባ ከብት ወደ አንጓላ እያጓጓዘች እዳዋን እየከፈለች መሆኑን ጋዜቲ አንጉላ የተባለ አንጎላ የሚገኝ ጋዜጣ አስነብቧል።
እሰከ አሁንም 1,500 ላሞችን የላከች ሲሆን በአጠቃላይ እዳዋን እንዲያጣጣ 75,000 ከብት በስድስት አመት ውስጥ ወደ አንጎላ ለመላክ ተስማምታለች።
የአንዱ ከብት ዋጋም በ1,300 ዶላር እዳ እንደሚሰርዝ ሁለት ሀገራት ያደረጉት ስምምነት ያሳያል።
አንጎላ ቁጥሩ እየተመናመነ የመጣውን የከብት ቁጥሯን ለመተካት ከቻድ ጋር ያደረገችው በቁም በከብት እዳን መቀበል ስምምነት ጠቃሚ ውሳኔ ነው ብላለች ።
ቻድ ወደ 90 ሚልየን የሚቆጠር የቀንድ ከብት ያላት ሲሆን የሀገሪቱ 30% የውጭ ንግድም የሚገኘው ከዚህ ዘርፍ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *