ራይድ በኤሌክትሪክ የምትሰራ ተስላ ኤስ የተባለች መኪናን ወደ ኢትዮጵያ አስገብቷል

የራይድ ትራንሰፖርት ቴክኖሎጂ ኩባንያን የሚያስተዳድረው ሀይብሪዲ ዲዘየን ተስላ ኤስ የተባለችውን የኤሌክትሪክ ሞዴል መኪና ወደ ሀገር ውስጥ ካህኖስ በተባለ ኢምፖርት ትሬድ ድርጅትአማካኝነት አስገብቷል።
መኪናዋ በአንድ ሙሉ ቻርጅ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ትጓዛለች።
የመጀመርያ የገባችው መኪና ለሀይብሪድ ዲዛየን ድርጅት አገልግሎት ስራ ላይ የዋለች ሲሆን በቀጣይ ግን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አካላት በተግባር እየነዱ እንዲፈትሿትና የኤሌክትሪክ መኪናን ጥቅም እንዲረዱ ብሎም በሂደት ኢትዮጵያ ወደዛ አቅጣጫ እንድታመራ ታቅዷል ስትል የራይድ ትራንሰፖርት ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ለፊደል ፖስት ተናግራለች።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *