በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ምርጫ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን በቦርድ ሊቀ መንበር የሚመሩት አቶ ካሳሁን ጎፌ (የኦሮሚያ ገቢዎች ባለ ስልጣን ሀላፊ) ፣የቦርድ አባሎች ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ( የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ) ሌሎች ስድስት የቦርድ አባሎች በስርአቱ ተሰብስበው ውሳኔ ባለማሳለፍቸው አዲስ የተጠናው የደሞዝና የሰራተኞች መዋቅር ተግባራዊ እንዳልሆነ ጋዜጠኞቹ ለፊደል ፓስት ተናግረዋል።
እንደጋዜጠኞቹ ገለፃ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና( ኢዜአ) ፕሬስ ድርጅት ፓርላማ በቦርድ የራሳቸውን ጉዳይ እንዲፈፅሙ እና ተጠሪነታቸውም ቀጥታ ለፓርላማ እንዲሆኑ ቢያደርግም የደሞዝና የሰራተኛ መዋቅር አስጠንቶ ተግባራዊ ያደረገው ኢዜአ ብቻ ነው ብለዋል።
በደሞዝ መዋቅሩ መዘግየት ምክንያት የለቀቁ ሰራተኞችም አሉ ብለዋል ።
ቦርዱም ይሄን አይቶ የተጠናውን መዋቅር አፅድቆ ወደ ስራ እንዲገባ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከ100 በላይ ጋዜጠኞቹና ፎቶ ግራፈሮቹ በአዲስ ዘመን፣ በበሬሳ፣ በሄራልድና፣ በአልአለም ጋዜጦችና በዘመን መፅሄት ላይ በአማረኛ፣በኦሮመኛ፣በእንግሊዘኛ እና በአረበኛ በሚሰራጩ የሚድያ ህትመቶች ውጤት ላይ ይሰራሉ።