“የግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ የፈረሰው ስራ አስኪያጁ ምሶሶውን በማስፈረሳቸው ነው “- ሰራተኞች


ማክሰኞ ህዳር 23 ቀን ስምንት ሰአት ገደማ 73 አመት የቆየው የግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ በእርጅና ምክንያት ሳይሆን የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ገብረፃድቃን አባይ አዳራሹን የያዘውን ምሶሶ እንዲፈርስ በማድረጋቸው ነው ሲሉ ሆቴሉ ላይ ረጅም ጊዜ የሰሩ ሰራተኞች ለፊደል ፓስት ተናግረዋል ።
” አዳራሹ ማክሰኞ ከመፍረሱ በፊት ሰኞ ስብሰባ አከናውኗል ።ምንም ችግር አልነበረበትም። አዳራሹን ከዳሽን አዳራሽ ጋር ለመቀላቀል ስለተፈለገ የተወሰኑ ምሶሶዎች አስቀድመው ፈርሰው ነበር ።ሆኖም ግን አዳራሹን የተሸከመውን ምሶሶ ስራ አስኪያጁ መፍረስ አለበት ሲሉ ተው ይሄ ምሶሶ ከፈረሰ አዳራሹ ይደረመሳል ብለን ነገርናቸው ።ፍቃደኛ ለመሆን አልቻሉም ። ምሶሶውን በገዛ ፍቃዳቸው አስፈረሱት ።በዚህም ምክንያት ጥንታዊው አዳራሽ ፈረሰ ። “በማለት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት ሰራተኞች ተናግረዋል።
አቶ ገብረፃድቃን በሰጡት መልስ” ይሄ በፍፁም ውሸት ነው አዳራሹ የቆየ ስለነበረ በራሱ ነው የወደቀው ይሄንም የለገሀር ፓሊስ ጣቢያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባቢርያ በፅሁፍ አረጋግጦልናል ብለዋል ።
ሰራተኞቹ እንደሚሉት ፓሊስ አዳራሹ ከፈረሰ በኋላ ነው የተገኘው ምንም የጂኦሎጂካል እና የኢንጀነሪንግ ቡድን ሳይዝ አዳራሹን በተፈጥሮ ነው የፈረሰው ማለት ስህተት የሆነ አካሄድ ነው በማለት የፓሊስን ሪፖርት ተቃውመዋል።
ፊደል ፓስት ሆቴሉ ኢንሹራንስ የገባበትን የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን ጠይቆ እንደተረዳው ሆቴሉ የመብረቅና የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ብቻ ስለገባ ኢንሹራንስ ሊከፈለው አልቻለም ነገር ግን እንደ ቆየ ደንበኝነታቸው ካሳ ሳይሆን በድጋፍ መልኩ የተወሰነ ብር ለመስጠት የአደጋውን መንስኤ የመሀንዲሶች ቡድን አዋቅረን እያጣራን ነው ።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ያጠናው ጥናት ደግሞ ሆቴሉ ድንገተኛ በሆነ ነገረ ተደረመሰ ይበል እንጂ ሆቴሉ በምን ምክንያት እንደተደረመሰ አይገልፅም ።

የፈረሰው ሳባ አዳራሽ ከ500 በላይ ሰዎችን የሚይዝ ስፋት የነበረው ሲሆን የውስጠኛው የጣሪያ ግድግዳ ላይ የንግስትን ሳባ ታሪኮች የሚያወሱ ስእሎች ነበሩት።






One thought on ““የግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ የፈረሰው ስራ አስኪያጁ ምሶሶውን በማስፈረሳቸው ነው “- ሰራተኞች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *