በ2012 በጀት አመት 19 ቢልየን ብር ለማትረፍ ያቀደው የኢትዮጰያ አየር መንገድ ግሩፕ አስከ ታህሳስ 30,2012 ባለው ስድስት የበጀት ወራቶች ውስጥ 7.82 ቢልየን ያልተጣራ ትርፍ አግኝቷል።
በተጠቀሰው ጊዜ አየር መንገዱ 67. 83 ቢልየን ብር የሰበሰበ ሲሆን በበጀት አመቱ ማጠናቀቂያ 155 ቢልየን ለመሰብሰብ አቅዶም አየሰራ ይገኛል።
አየር መንገዱ ይሄን ገቢና ትርፍ ያገኘው በዓለም አቀፍና በሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርት ሰዎችና ዕቃ በማጓጓዝ፣ የኤርፖርት አገልግሎትና የሆቴል መስተንግዶ በማቅረብና እንዲሁም የአቬሽን ሥልጠና በመስጠት ነው።
በአሁኑ ሰአት አየር መንገዱ በ83 ሀገራት ላይ 129 አለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት።
አየር መንገዱ ትልቁ ገበያ ምእራብ አፍሪካ እና ቻይና ሲሆን በቻይና የተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ግን የአየር መንገዱን የቻይና በረራ ላይ በገበያው ላይ ተወሰነ ችግር ፈጥሮበታል።
በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት በግማሽ በጀት አመት 11.79 ቢሊዮን ብር አስገኝቷል።ያልተጣራም ትርፍ 1.23ቢልየን ብር ያስገኘ ሲሆን ይሄም ከእቅዱ አንፃር ሲታይ የ4 % ብልጫ አለው ።