አለም አቀፉ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ሻራን ቡሮው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መብት ጥሰት አየተፈፀመ አንደሚገኝ ገልፀው ይሄንንም ጉዳይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ መፍትሄ አንዲሰጡለት በድብዳቤ አሳውቀው መልስ እየተጠባበቀ መሆኑን ፊደል ፖስት ለመገንዘብ ችሏል።


ዋና ፀሀፊዋ በደብዳቤያቸው አንዳመለከቱት የኢትዮጵያ አየርመንገድ መሰረታዊ ሰራተኞች ማህበርን ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የሺዋስ ፈንታሁን-( የማህበሩ ሊቀመንበር) ፣ ማርቆስተሱወርቅ ( የማህበሩ ም/ ል ሊቀመንበር) ፣ ተከስተ ካሴ-( የማሀብሩ ም/ፀሀፊ) ፣ ሰምሀር አርአዶም (የማህበሩ ምክር ቤት አባል) ፣ አልታሰብ ብርቁ (የማህበሩ ሒሳብ ሹም)፣ ካፒቴን ሀይለሚካኤል ዳመና (የማህበሩ ኦዲተር ) አንዲሁም ካፒቴን አዲሱ ወልደሚካኤል (የማህበሩ አባል )ባልተገባ አኳኋን ከደርጅቱ ከስራ አንደታገዱ ገልፆ ይሄም የሰራተኛ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ደርጅት እንዳለ አንደሚያሳይ ገልፀዋል።
የማህበሩን እየተፈፀመበት ያለውን የመብት ጥሰት ለማስቆም በኢትዮጵያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አደራዳሪነት ኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን ፣የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ሰራተኞች ፊዴሬሽን፣የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር እና የአየር መንገዱ ተወካዮች በተገኙበት በጋራ ውይይት ቢያደርጉም አየር መንገዱ ውስጥ አሁንም ሰራተኞች መብታቸውን ስለገለፁ ከስራ እየተባረሩ አንደሚገኝና ይሄም አለም አቀፉ የሰራተኞች መደራጀትና መብት መግለፅን ህግ የተፃረረ መሆኑን አመልክተዋል።
ዋና ፀሀፊዋ ኢትዮጵያ የሰራተኞችን መብት የሚያስከበር ህግ አንዳላት ገልፀው ይሄንንም ተግባራዊ በማድረግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ላይ የተፈፀመውን የመብት ጥሰት በህግ አግባብ አንዲዳኝበት ለጠ/ ሚንስትሩ በድብዳቤያቸው አሳስበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአስተዳደሩ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ እምነት እንዳለቸው ገልፀዋል።
አለም አቀፉ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (International Trade Union Confederation – ITUC) ኢትዮጵያን ጨምሮ በ163 አለም ሀገራት 207 ሚልየን ካቀፉ የሰራተኛ ማህበራት ጋር አብሮ ይሰራል።