ከ7 አስከ 10ኛ ክፍል ያሉ ትምህርቶች በዲቪዲ ለገበያ ሊቀርቡ ነው



ስኮላር ኢ ፐብሊሸር የተባለ የግል ማህበር ከ7ኛ እስከ 10ኛ ያሉ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርቶችን በዲቪዲ አምርቶ ኢ ፋኖስ በተባለ የምርት መጠሪያ በገበያ ላይ ሊያሰራጭ መሆኑን አስታውቋል።
ዲቪዲዮዎቹ የትምህርት መስጫ፣ የማጠቃለያና የጥያቄና መልስ ክፍል ፣የማጠቀሻ መፅሀፈት ፣ ላብራቶሪና ጭብጥ ሀሳቦችን በቪድዮና በምስል ያቀርባሉ ሲሉ የማህበሩ አመራሮች ለጋዜጠኞች
ዛሬ ሀሙስ የካቲት 12 ለጋዜጠኞች በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።ዲቪዲዎችም በትምህርት ቤቶችችና በትምህርት መሳሪያ መሸጫ ቤቶች በኩል የሚከፋፈሉ ሲሆን የአንድ ዲቪዲ ዋጋም 98 ብር እንደሆነ ገልፀዋል።
ማህበሩ ከ11ኛ እስከ 10ኛ ያሉ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርቶችን በዲቪዲ ለማሰራጨት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልፇል።
ከኬጂ አስከ ስድስተኛ ያሉ እንግሊዘኛ፣የአማረኛ ቋንቋና የአካባቢ ሳይንስ ትምህርቶችን ተረቶችን ፣ጨዋታዎችን ጭምር ከመልቲሚድያ መልክ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *