አለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ የአለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ለ25 ደሀ ሀገራት 500 ሚልየን ዶላር የብድር ስረዛ አድርጓል ።
የተቋሙ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስ ክሪስታሊና ጆርጂቪያ በሰጡት መግለጫ የብድር ቅነሳው ዋና አላማ ሀገራቱ የሚከፍሉትን ብድር ለህክምና እና ለሌላ ወሳኝ ችግሮቻቸው እንዲያውሉት በማሰብ ነው።
ብድር ከተሰረዘላቸው ሀገራት ፣ቤኒን፣ቡርኪና ፋሶ፣ሴንትራል አፍሪካሪፐብሊክ ፣ቻድ ፣ኮሞሮስ ፣ኮንጎ ፣ጋምቢያ፣ጊኒ፣ጊኒቢሳው፣ሀይቲ፣ላይቤሪያ፣ማዳጋስካር፣ዶሚኒክ ሪፑብሊክ ፣ማላዊ፣ማሊ፣ሞዛምቢክ ፣ኔፓል፣ኒጀር ፣ሩዋንዳ፣ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንስፔ፣ሴራሊዮን፣ሶሎሞን አይላንድስ ፣ታጃኪስታን እና የመን እናአፍጋኒስታን ናቸው።