ብሔራዊ ሎተሪ በፎርጅድ ሎተሪ ሰባት ሚልየን ብር ለአንድ ግለሰብ ሊከፍል ጫፍ ደርሶ ነበር


የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር እጣ የወጣላቸውን ባለ እድለኞች ከፍያ የሚፈፅመው የአሸነፉበትን እጣ ትኬት ይዘው አስተዳደሩ ጋር ከቀረቡ ወዲያው ሳይሆን ከ15 ቀን በኋላ ነው የሚል መረጃ ለፊደል ፓስት ሰለደረሰ መረጃውን ለማጣራት የፊደል ፓስት ዘጋቢ የአስተዳደሩን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስን ነዋይን ጠይቆ ነበር።
ፊደል ፓሰት: ከዚህ ቀደም ሰዎች ሎተሪ ጠዋት ቢደርሳቸው ከሰአት ብር ያወጡ ነበር ይሄ አሰራር ተቀይሮ ባለእድለኞች ሁለት ሳምንት ድረስ ብር ለመቀበል እየጠበቁ ይገኛሉ ።ይሄ ለምን ሆነ?
አቶ ቴዎድሮስ: እውነት ነው ።እንደድሮ ወዲያው አንሰጥም ።ይሄ የሆነበት ምክንያት ትንሽ ቆየት ቢልም የሰባት ሚልየን ብር ሀሰተኛ ትኬት ወደ እኛ መጥቶ አጭበርባሪው ግለሰብ ሊከፈለው ጫፍ ደርሶ ስለተነቃበት ተመሳሳይ ነገሮች እንዳይፈፀሙ አንድ እድለኛ አሸናፊ ቁጥር ይዞ ከመጣ ትኬቱ የሚታተምበት ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት ዳግም ተልኮ እውነተኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው አሸናፊው የባንክ ቼክ ከእኛ የሚወስደው።
ፊደል ፓስት : አስቲ ስለተፈፀመው ወንጀል በደንብ ቢያብራርሉን?
አቶ ቴዎድሮስ ፣አንድ ወጣት ሰባት ሚልየን ብር ደርሶኛል ብሎ መጣ ።እኛም ተቀበልነው ።ሀሰተኛ ትኬት ቢሆንም የእኛን ፍተሻ አለፈ።ለልጁ ብር ለመክፈል ዝግጅት ላይ እንዳለን ከአዳማ ተደወለልን ።በተመሳሳይ ቁጥር በአዳማም አሸናፊ እንዳለ ተነገረን ።በዚህ ጊዜ አዲስ አበባ እኛ ጋር የመጣው ልጅ የውሀ ሽታ ሆኖ ቀረ።ስናጣራ የአዳማው ትኬት ነው ትክክለኛ አሸናፊ ሆኖ የተገኘው ።በዚህም ምክንያትአሸናፊ የሎተሪ ትኬቶችን ብርሀንና ሰላም ልከን ካላጣራን አንከፍልም ።ለዚህም ማጣራት የተወሰኑ ቀናቶች ይፈጃል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *