ቅርስ የሆነው የራስ ሙሌጌታ ቤት ደህንነት ነን ያሉ ሰዎች “አንወጣም ” በማለታቸው ሊታደስ አልቻለም



በአዲስ አበባ ቅድስተ ማርያም አካባቢ የሚገኘውና ዘጠና አመት ያስቆጠረው የራስ ሙሉጌታ ( አባ ገስጥ ቤት) ደህንነት ነን አንወጣም ስላሉኝ ቤቱን ላድስ አልቻልኩም ሲል የከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ቅሪታውን ገለፀ።

የቢሮው የቅርስ ጥበቃ ክፍል ዛሬ ለፊደል ፓስት እንደተናገረው ትናንት ሐሙስ ወደ ሰባት የሚጠጉ ፓሊሶችን ይዞ ወደ ቤቱ ቀን ስምንት ሰአት ገደማ ቢዘልቅም በውስጡ ያሉ ሰዎች ግርግር መፍጠራቸውንና ፓሊስም ሑከት ላለመፍጠር ሲል ቦታውን ለቆ ሂዷል ብሏል።
ቢሮውም ለከተማዋ ፓሊስ ኮሚሽን አቤቱታ አቅርቦ ምላሽ አየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተናግሯል።

እንደ ቢሮው ገለፃ ቤቱ በደርግ ግዜ የፓሊት ቢሮ ሆኖ ሲያገለግል እንደነበረና ከዛም ት/ቤት ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ከቅርብ አመታት ጀምሮ ግን የደህንነት ሰዎች ሲጠቀሙበት እንደነበረ ገልፇል።
ሆኖም ግን ያለምንም ህጋዊ ዶክመንት ወደ ስምንት የሚጠጉ አባወራዎች ከነቤተሰቦቻቸው 760 ካሬ ሜትር ገደማ የሆነውን መሬትን ይዘውት የደህንነት ስዎች ነን በሚል ምክንያት አንወጣም በማለታቸው ታድሶ ለቱሪስት አገልግሎት አንዲሰጥ የታሰበውን በህገወጥ መልኩ መያዛቸውን አስረድቷል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የሚገኘው በግንብ የተሰራው ባለ አንድ ፎቅ ቤት የሰሩት ራስ ሙሉጌታ የመጀመሪው የገንዘብ ሚኒስቴር ሲሆኑ የካቲት 19,1929 ማረፋቸው የታሪክ ማህደራቸው ይናገራል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *