የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ስካይ ላይት ሆቴል በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተገመገመ በኋላ ባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ተሰጥቶታል።
የዛሬ አመት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተመርቆ ሰራ የጀመረው በቦሌ አየር ማረፍያ ጎን የሚገኘው ሆቴል ለግንባታ 65 ሚልየን የአሜሪካ ዶላር የፈጀበት ሲሆን 373 የመኝታ ክፍሎች ሲኖሩት በአንዴ 2,000 ተሰብሳቢዎችን የሚያስተናግድ የስብሰባም አዳራሽ አለው።