የ83 አመቱ የሮማው ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ሰሞኑ ሳልና ብርድ ስለተያባቸው በኮሮኖ ቫይረስ ተጠቅተዋል በሚል ስጋት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 24 እንዳደረጉና ከበሽታውም ነፃ እነደሆኑ የጣሊያኑ ኢል ማሳጂሮ ጋዜጣ አስነብቧል።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ፖፕ ፍራንሲስ የፋሲካን ፃም አስመልክቶ ንስሀ ስለመግባት ፣ይቅር ስለማለት ፣ስለ አለም ሰላምና ስለ እራስ ሰለ መፀለይ በየአመቱ በሚደረገውና ባለፈው እሁድ ተጀምሮ ለስድስት ሳምንት በሚቆየው ፕሮግራም ላይ ተገኘተው ተደጋጋሚ ሳል የተያባቸው ሲሆን ጳጳሱ አሟቸው ቀሪውን ፓሮግራም በደቡብ ሮም በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ሆነው ነው የተከታተሉት ።በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በጋዜጣው የተጠየቁት የቫቲካን ቃለ አቀባይ ማት ብሩኒ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በጣልያን አስከ አሁን 52 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ሲሞቱ ከ2,000 በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል።