የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ዛሬ በፌስቡክና በቲዊተር ገፆቻቸው በጋሩት መልእከት ባቋቋሙት መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ አመራሮች በአየር መንገዱ የስራ ሀላፊዎች ያለ አግባብ ከስራ መታገዳቸውን ገልፀው የሀገሪቱን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን የታገዱትን ሰራተኞች ወደ ስራ እንዲመልሷቸው ጥሪ አቅርበዋል።

” የተከበሩ አብይ አህመድ ዛሬ የሰራተኞች ቀን ነው ።የእኛም ቀናችን ነው ።በዛሬው ቀን ለፍትህ ሲሉ ለእኛ ለተዋደቁና ከስራ የተባረሩ ሰራተኞች ድምፅ የምናሰማበት ነው።እርሶም አንደሚሰሙን ተስፋ እናደርጋለን በማለት ” በማህበራዊ ገፅ ላይ ፅፈዋል።
ከስራ ከታገዱት ውስጥ የማህበሩ ዋና ፀሀፊ ካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን ፣ምክትል ሀላፊ ማርቆስ ተሱወርቅ ፣ተከስተ ካሴ- ም/ፀሀፊ ፣ የማህበሩ ምክር ቤት አባል ሰምሀር አርአዶም ፣አልታሰብ ብርቁ-የማህበሩ ሒሳብ ሹም እንዲሁም ሀይለሚካኤል ዳመና የማህበሩ ኦዲተር ይገኙበታል።