” ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ከከፈተች ከስምንቱ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ነው የምትጣላው ” ዶ/ር ግርማ ግዛው

” ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ከከፈተች ከስምንቱ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ነው የምትጣላው ” አለም አቀፍ የህግ ምሁሩ ዶ/ር ግርማ ግዛው

ሰሞኑን ግብፅ ከሱዳን ጋር ወታደራዊ ልምምድ አንዲሁም ከኬንያ ጋር እና መለስ ቀለስ እያለች ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ይገኛል ። ይሄ የግብፅ አንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በመጠኑም ቢሆን አስግቷል።
የፕሪቶር ቢዝነስ ኮሌጅ ፕሬዝዳንትና አለም አቀፍ የህግ ምሁሩ ዶ/ር ግርማ ግዛው ኮሌጃቸው በአባይ ጉዳይ ላይ ምሁራንን ጋብዞ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ውይይት አርጎ ነበር ።
“ፊደል ፖስትም ግብፅ ጦርነት ታነሳ ይሆን? ዶ/ር ግርማ ግዛውን ጠይቋቸው ነበር ።

” በፍፁም ጦርነት ውስጥ ይገባሉ ብዬ አልገምትም ። አንድን ሉዐላዊ የሆነ ሀገር ከራሱ የሚመነጭ ወንዝን ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ በፍትሀዊነት በመጠቀሙ ጦርነት ልክፈት ብትልም አለም አቀፍ ህግ ራሱ አይደግፍህም “
” የአባይ ጉዳይ ችግር የሚመነጨው ከእራሳቸው ከሱዳንና ግብፅ ነው ። ለወንዙ ከ85% ከመቶ በላይ ድርሻ ያላትን ኢትዮጵያን ሳያሳትፉ ለእራሳቸው ብቻ የሚፈሰውን የወንዙን ውሃ መከፋፈላቸው አለም አቀፍ ህግን ጥሰዋል “

” አለም አቀፍ ህግ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ፍትሀዊ ክፍፍል ይኑራቸው አለ አንጂ ሊያውም የወንዙ መነሻ ያልሆኑ አገሮች ብቻቸውን ይውሰዱ አላለም ።”
” አንድ ሰው ከቤቱ ውሃ ካለ ቢጠማው ጎረቤቱ ውሃ ቢቸግረው መጀመሪያ እራሱ ጠጥቶ ከረካ በኋላ የተረፈውን ለጎረቤቱ ይሰጠዋል ።ኢትዮጵያ ግን ራሷ ተጠምታ ግብፅን ነው ያጠጣችው ። አሁን እራሴ ልጠጣ ስትል መኮነን የለባትም መታገዝ አንጂ “

” ግብፆች ይሄን እውነታ ያቃሉ ። ህግ እያለ ህግን ጥሰው ነገሮችን በሀይል ላስከበር ቢሉ ዋጋ ይከፍላሉ ።የላይኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ኮንጎ፣ ብሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአባይ ወንዝ በእነሱም ስለሚያልፍ ነገ ብዙ ነገር መስራት ይፈልጋሉ ። ግብፅ ይሄ አይሆንም ብላ የህዳሴን ግድብ ላይ ጦርነት ብትከፍት እነሱንም በተዘዋዋሪ እንደ ኢትዮጵያ ግድብ ብትሰሩ አትጠቀሙም እያለች ስለሆነ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ፀብ ውስጥ ነው ምትገባው ። “
” ብቻዬን ልብላ የሚባልበት ዘመን አይደለም ። ግዜው በጋራ ተስማምተክ በፍትሀዊ ክፍፍል በሰላም የምትካፈልበት ግዜ ነው በማለት ተናግረዋል ።

ዶክተር ግርማ በአባይ ጉዳይ የምሁራን ተሳትፎ አናሳ መሆንና በውሃው ላይ የሚደረጉ አውደ ጥናቶችና ውይይቶች እጅግ አነሳ ናቸው ብለዋል ።
” ግብፅ በቅርብ አመታት ውስጥ በአባይ ጉዳይ ብቻ ከ640 በላይ አውደ ጥናቶችና ውይይቶችን አድርጋለች ኢትዮጵያ 30 ማድረጓንም አንጃ? ! የአባይ ጉዳይ ትልቁ እውነት እኛ ጋር ሆና ሳለ በምርመርርና በጥናት የተደገፈ ለአለም ህዝብ እያቀረብነው ያለው ነገር ትንሽ ነው። ስለ አባይ ሲነሳ በዘፈንና በሰላማዊ ሰልፍ ብቻ አይደለም ተቆርቋሪነታችን ማሳየት ያለብን ።አለም አቀፍ ህብረተሰብ ጋር የሚደርሱ ተከታታይ ጥናቶች ውይይቶች በመንግስትም በግል ባለሀብቱም በኩል መሰራት አለባቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ዶክተር ዱጋሳ ሙሉጌታ ጥናት ሲያቀርቡ

በዛሬው ውይይት ላይ ፅሁፍ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጀ የጥራት ማረጋገጫ ደይሬክተር ዶክተር ዱጋሳ ሙሌጌታ “ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ የሚያክል ረጅም ወንዝ ውሃ የሚመነጭባት ሀገር ሆና
ውሃ እያመነጨች የተበደለች ብቸኛ ሀገር ናት “
” ሀገርክ ላይ በመነጨ ወንዝ አትጠቀምም ማለት በምን አይነት ስሌት አያስኬድም ። ግድቡ አንደ ኢትዮጵያ ላለ ታዳጊ ሀገር ለብዘዎች ከድህነት መውጫ መንገድ ነው ። በሀይል አቅርቦት አለመኖር ኢንደስትሪ አከመክፈት ፣በመብራት አለመኖርም ዜጎችን በጨለማ ማደር አይገባቸውም ። አባይ ወንዝን ሌሎችንም በመጠቀም ከድህነት ማምለጥ አለብን ።
” ህዝብና መንግስት እየተናበበ ፣እቅድ እያወጣ ፣ምርምርና ጥናት እያካሄደ ፣ፖሊሲ እየቀረፀ በዘርፉ ብዙ ምሁራን እያፈራ ነገሮችን በጥራትና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስራት ” ይገባዋል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *