የፔሌ ሞት የእግር ኳሱን አለም ሀዘን ውስጥ ከቶታል

ብራዚላዊው ድንቅ ተጫዋች ኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ ( ፔሌ) በ82 አመቱ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ከተረጋገጠ በኋላ የእግር ኳስ አለም በሀዘን ላይ ነው።

ፔሌ ከኮሎን ካንሰር ጋር የታመመ የነበረ ሲሆን በህዳር ወር መጨረሻ በሳኦ ፓውሎ በሚገኘው አልበርት አንስታይን ሆስፒታል ገብቶ ክትትል እያረገ ነበር።

ዶክተሮች በሽታው እየተባባሰ መሆኑን በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ አስታውቀዋል።
የሶስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ማምሻውን ቤተሰቦቹ እንደተከበበ ህይወቱ አልፏል።

ፔሌ ሶስት ሚስት ያገባ ሲሆን ሰባት ልጆም ወልዷል።

በተጫዋችነት ዘመኑ ድንቅ ግብ አስቆጣሪ የነበረው ፔሌ በብዙዎች ዘንድ ከምርጥ የእግርኳስ ተጫዋቾች አንዱ ነው በማባል በብዘዎች ተመርጧል።

በፈረንጆቹ 1958 በስዊድን በተደረገው ውድድር በ17 አመቱ የመጀመሪያውን የአለም ዋንጫ አግኝቷል።

ፔሌ በ1956 የ15 አመት ታዳጊ እያለ በሳኦ ፓውሎ ግዛት የባህር ዳርቻ ክለብ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በብራዚል በሚገኘው ሳንቶስ የክለብ ተሰልፎ ተጫውቷል።

በጎል አግቢነቱ የሚታወቀው ፔሌ በ92 ጨዋታዎች 77 ጎሎችን በማስቆጠር ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን በ ፈረንጆቹ 1971 ራሱን አገለለ።

ፔሌ የክለብ የእግር ኳስ፣ ህይወቱን በኒውዮርክ ኮስሞስ በ1977 አጠናቀቀ።

በድህረ-ጨዋታ ዘመኑ፣ ፔሌ በ1992 የተባበሩት መንግስታት የስነ-ምህዳር እና የአካባቢ አምባሳደር እና በ1994 የዩኔስኮ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነው ተሹሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *