የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ለመሰብሰብ ካቀደው 146.9 ቢሊየን ብር 149.2 ቢሊየን ብር በመበሰብሰብ የእቅዱን 102 በመቶ ማሳካት መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም አፈፃፀሙ ከባለፋው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ21.6 ቢሊየን ብር ወይም የ17 በመቶ እድገት ማሳየቱንና የተሰበሰበው ገቢ ከገቢ አርዕስቶች አንፃር ሲታይ ከሀገር ውሥጥ ገቢ 93.3 ቢሊየን ፣ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 55.7 ቢሊየን እና ከብሔራዊ ሎተሪ ስተዳደር የተጣራ ትርፍ 130 ሚሊየን ብር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ጠንካራ የሆነ የድጋፍና ክትትል ስራዎች መሰራታቸው ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፍ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ መደረግ ፣ ከቅ/ፅ/ቤቶች ጋር በየሳምንቱ ጠንካራ የግምገማና የልምድ ልውውጥ እንዲሁም ለስራ እንቅፋት የሆኑ ችግሮች ከስር ከስር እየተፈቱ መሄዳቸው የተያዘው እቅድ ሊሳካ እንዳስቻለ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አክለው ማህበራዊ ሀላፊነትን ከመወጣት አንፃርም ባለፉት ስድስት ወራት በሚኒስቴር መ/ቤቱና በተጠሪ ተቋማት የሚሰሩ አመራርና ሰራተኞች ከደሞዛቸው ከ800ሺ ብር በላይ በማዋጣት 209 ተማሪዎችን በቋሚነት እየረዱ እንደሚገኙና ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክትም ከ58.3 ሚሊየን ብር በላይ ከደሞዛቸው እየተቆረጠ ገቢ እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል::
እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ442.7 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ እንደተደረገአንስተዋል፡፡