የዶሮ መኖ ዋጋ ንረቱ በዚሁ ከቀጠለ ለአብዛኞዎቹ ኢትዮጵያውያን ዶሮ የቅንጦት ምግብ ሊሆን ይችላል ተባለ

በስምንት ወር ውስጥ የዶሮ መኖ ዋጋ በኩንታል ከ1,550 ወደ 2,880 ያደገ ሲሆን በርካታ ዶሮ አርቢዎች መኖ እየተወደዳባቸው ከስራ እየወጡ መሆኑን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር ለፊደል ፖስት ገልፇል።

በዶሮ መኖ ዝግጅት ውስጥ በግብአትነት ከ90% ድርሻ ያላቸው ፋጉሎ ፣በቆሎ እና ፉርሽካ ዋጋቸው በአንድ አመት ውስጥ በእጥፍ ጨምሯል ።
በአሁን ሰአት ፋጉሎ በኩንታል 4,200 ብር ፣ በቆሎ 2,100 ብር አንዲሁም ፉርሽካ 1,800 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ሚሊዮን ለፊደል ፖስት እንድተናገሩት የዶሮ የመኖ እየተወደደ በመምጣቱ ብዙ ዶሮ አርቢዎች ከስራ እየወጡ ነው ይሄም ስጋት ፈጥሮብናል ብለዋል።
” ከዚህ ቀደም አርቢዎች ጫጩት ለመረከብ አምሰት ወር ድረስ እየጠበቁ ከጫጩት ማስፈልፈያ ድርጅቶቸ ይረከቡ ነበር ።አሁን ተረካቢ እምብዛም የለም ። አርቢው ከስራ በወጣ ቁጥር ለገበያ የሚቀርበው ዶሮ ትንሽ ይሆናል ።ያ ደግሞ አቅርቦቱን በማሳነስ የዶሮ መግዣ ዋጋን ከፍተኛ ያደርገዋል።

” እንቁላል በአመት የሁለት ብር ጭማሪ እያሳየ ነው ። በአሁን ላይ ከሰባት ብር ላይ አንድ እንቁላል እየተሸጠ ይገኛል ።የዶሮ ዋጋም እየጨመረ ነው ። መኖ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ካልተሰራ ዶሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የቅንጦት ምግብ መሆኑ አይቀሬ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።
ሁለት ግዙፍ የዘይት ፍብሪካዎች በቅርቡ ቢከፈቱም ለዶሮዎች መኖ የሚሆን ፍጉሎ እያቀረቡ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *