የኮሮና ቫይረስ ስጋት በአዲስ አበባ የአፍ ጭንብል ዋጋን አምስት እጥፍ አሳድጎታልበኢትዮጵያ መንግስት በኩል የኮሮና ቫይረስ ዛሬ በአንድ ጃፓናዊ በኩል ኢትዮጵያ እንደተገኘ የተነገረ ሲሆን ለአጭር ሰአት የምታገለግለው ከአቧራ እና የሰዎች ትንፋሽ ወደ አፍና አፍንጫ እንዳየይገባ የምትከላከለው የአፍ ጭንብል በሳምንት ግዜ ውስጥ ከአምስት ብር ወደ 25 ብር ማደጉን ፊደል ፖስት ከፋርማሲዎች ያገኘው መረጃ ይጠቁማል ። ጭንብሉ በእጥረት ምክንያት ዋጋው መወደዱን ፋርማሲዎች ሲናገሩ ተጠቃሚዎች ደግሞ ዋጋው ሆን ተብሎ በኮሮና ቫየረስ ሰበብ እንደተወደደ ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *