የእግር ኳስ ኮከቡ ክላይን ማፔ በኮሮና ቫይረስ ቢጠረጠርም በምርመራ ነፃ ሆኗል



እንደ ሊኪፒ ጋዜጣ ዘገባ የ21 አመቱ የፈረንሳዪና እና የፓሪሴን ዠርሜን አጥቂ ክላይን ማፔ ባለፉት ሁለት ቀናት የጉሮሮ ህመም ከሜዳ ልምምድ ያስቀረው ሲሆን ማክሰኞ ምሽት በተደረገለት የመጀመርያው ምርምራ የኮሮኖ ቫይረስ እንደያዘው ቢነገረም ቀጥሎ በተደረገለት ምርመራ ግን ተጫዋቹ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን ተረጋግጧል ።ማፔ የፓሪሴን ዠርሜን ነገ እሮብ መጋቢት ሁለት ምሽት በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ከጀርመኑ ዶርቱሙንድ ጋር በስታንዳ አ ፍራንስ በሚደረገው ወሳኝ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ይሰለፋልም ተበሎ ይጠበቃል። ማፔ በዚህኛው የፈረንሳይ ሊግ 1 ውድድር አመት 18 ጎሎችን አስቆጥሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *