” የእነዋሪ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ጥቃት ሲደርስባት ፓሊስ ፈጣን ምላሽ አልሰጠም ” ፓስተር ሳሙኤልትናንት መጋቢት 1,2012 ዓ.ም ቀን 9 ሰአት በሰሜን ሸዋ ሞረትና ጅሩ ወረዳ እነዋሪ ላይ የምትገኘው የሙሉ ወንጌል አማኞች ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ስትዘረፍና ስትቃጠል ፓሊስ ፈጣን ምላሽ አልሰጠም ሲሉ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የሰሜን ማእከላዊ ቀጠና የቦርድ ሊቀመንበር ፓስተር ሳሙኤል ታፈሰ ለፊደል ፖስት ተናገሩ።
እንደ ፓስተሩ ገለፃ በቃጠሎውና በዘረፋው ቤተክርስቲያኗ 1.5 ሚልየን ብር አጥታለች ብለዋል።
” ከአስራኤል የመጡ ህክምና የሚሰጡ ቡድኖች ሀይማኖት አየሰበኩ ነው በሚል ምክንያት የተደራጁ ቡድኖች 20 አመት የቆየችውን ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት አድርሰዋል።
” ተደራጅተው ቤተክርስቲያኗን ለማጥቃት ሲመጡ ጥበቃው ድረሱልኝ ለማለት ወደ ላይ ጥይት ተኮሰ ።ጥይቱ ሲያልቅበት መሳርያውን ተቀብለውት ደበደቡት ።እሱንና ሶስት ፀሎት ላይ የነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት አድረሰዋል ። ቤተክርስቲያኗ ውስጥ የነበረ ጄኔሬተር ፣ፒያኖ እና ገንዘብ በመኪና አጓጉዘው እስኪወስዱ ፓሊስ አልደረሰም ።በመጨረሻ ቤተክርስቲያኗ ስትቃጠል ነው ፓሊስ የመጣው ።ይሄ በጣም ያሳዝናል ።” ብለዋል።
የተጎዱት ሰዎችም በአሁኑ ሰአት ደብረብርሃን ሆስፒታል እንደሚገኙ ተናግረዋል።

” ህክምና የሚሰጠው ቡድን ለሊት ወደ አዲስ አበባ ሄዷል ።አሳዛኙ ነገር ፓሊስ አንድም ሰው በወንጀሉ ላይ ጠርጥሮ አለመያዙ ነው ። አንድን እምነትን ከሌላ ከእምነት የሚያጋጩ ክፍሎች ላይ እርምጃ ቶሎ ካልተወሰደ ሌላ ችግር እየወለደ ነው የሚመጣው ” ብለዋል
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ፃድቁ አብዶ ለፊደል ፖሰት በስልክ እነደተናገሩት ይሄን ድርጊት የፈፀሙት ሰዎች ከጀርባቸው የፓለቲካና አጀንዳ ያላቸውየሐይማኖት እኩልነትን የማያከብሩ ናቸው ብለዋል
” በደረሰኝ መረጃ ፓሊስ ወገንተኝነት አሳይቷል ።ይሄ ብዙ ግዜ ምናገረው ነገር ነው አንድ አካባቢ ያሉ ጥቂት የሌላ እምነት ተከታዮች ሲበደሉ ፓሊስ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለበት ። ጥቃትም ሲደርስ የፍትህ አካሉ ህግ በማስከበር የሀይማኖት እኩልነትን ማስከበር አለበት ።በዚህ ላይ ብዙ ችግሮች አሉ።ችግሮቹ ዋጋ እያሰከፈሉን ማምለኪያ ስፍራዎችንእያቃጠሉ አማኞችን እያሸማቀቁ ” ናቸው ብለዋል።

እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና ለመስጠት
ያቀናው የሕክምና ቡድን 18 የውጪ አገር ዜጎች የተካተቱበት መሆናቸውን የከተማዋ ፓሊስ መምሪያ ዋና ኢንስፔክተር ወጋየሁ ቦጋለ ገልፀዋል።

የወንጌላዊያን አማኞች የነፃ ህክምና አገልግሎት ጎን ለጎን ከሆስፒታሉ አጠገብ ድንኳን ተክለው የህክምና አገልግሎቱን ለማግኘት የመጡትን የኃይማኖት ስብከትና የእምነት መፅሐፍ የማደል ስራ ላይ ስለነበሩ ነው ቃጠሎው የተከሰተው የሚል ፅሁፍም በማህበራዊ ሚድያ በኩል ከአካባቢው ነዋሪዎች መልሰ እየተሰጠበት ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *