የአፍሪካ ህብረት ማሊን ከህብረቱ አባልነት አገደ


በቅርቡ በማሊ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ማሊን ከህብረቱ አባልነት ማገዱን ይፋ አድርጓል፡፡

የአፍሪካ ህብረት አገሪቱን ከህብረቱ አባልነት ያገደው ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ በማሊ መፈንቅለ መንግስት መደረጉን ተከትሎ ነው፡፡

ማሊ በአፋጣኝ በአገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ስርዓት እንዲሰፍን እንድታደርግና በሲቪል የሚመራ መንግስት እንድታቋቁም ህብረቱ ጠይቋል፡፡

ህብረቱ በመፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን በትረ ስልጣን የያዘው ወታደራዊ ሀይል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወታደሮቹን ወደ ካምፕ እንዲመልስ ጠይቆ፤ ይህንን ተግባራዊ ካለደረገ ግን በማሊ ላይ ማእቀብ እንደሚጥል ማስጠንቀቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *