የአዘርባጃን ኤምባሲ “ብሔራዊ የመዳን ቀን”ን ሊያከብር ነው


አዲስ አበባ የሚገኘው የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ኤምባሲ ሰኔ 15 ቀን 2021 28ኛውን የ”ብሔራዊ የመዳን ቀን” ሊያከብር ነው ፡፡
ኤምባሲው እንዳስታወቀው ‘ብሔራዊ የመዳን ቀን’ የሃገሪቱ ብሄራዊ መሪ ሃይደር አሊዬቭ አዛርባጃንን ተጋርጦባት ከነበረው አስፈሪ የእርስ በእርስ ጦርነት ስጋት ለመታድግ ወደ ስልጣን የመጡበትን ቀን የሚዘክር ህዝባዊ በዓል ነው ፡፡
አዘርባጃን የሶቪየት ህብረት ውድቀትን ተከትሎ እኤአ በጥቅምት 1991 በድጋሚ ነጻነቷን ብትጎናፀፍም ስልጣን ለመያዝ በሚታገሉ በርካታ ሃይሎች ሽኩቻ ወደ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ትርምስ ገባች፡፡ በወቅቱ የነበረው የአዘርባጃን ሕዝባዊ ግንባር ፓርቲ አገሪቱን ወደ ብልፅግና ለመምራት ይቅርና ሰላምና አስተማማኝ የሕግ የበላይነት ማስፈን ያልቻለ ልፍሰፍስ ሆነ፡፡


በዚህ ምክንያት በአዛርባጃን የእርስ በእርስ ጦርነት አይቀሬ መሆኑን ብዙዎች ተነበዩ፡፡ ይሁንና ይህ ስጋት ብሄራዊ መሪው ሃይደር አሊየቭ የመላው አዛርባጃናዊያንን “ምራን” የሚል ተደጋጋሚ ግብዣና ተማጽኖ ተቀብለው ወደ ባኩ ከተማ እስከመጡበት ጊዜ ድረስ ብቻ ዘለቀ፡፡
የብሔራዊ መሪው እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆነው ከተመረጡ በኋላ የፕሬዚዳንቱን ባለሥልጣናት በመረከቡ በአዘርባጃን የተከሰተውን የእርስ በእርስ ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስቆም ቻለ፡፡ የአገሪቱንም ከመበታተን አደጋ ታደገ፡፡
ብሄራዊ መሪው በዚያው ዓመት ጥቅምት ወር በተካሄደው ሃገር አቀፍ ምርጫ አሸንፈው ለቀጣይ አስር ዓመታት አዛርባጃንን የሚያስተዳድሩ ፕረዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡ ሃይደር አሊየቭ ግዙፍ አገራዊ ዕቅዶችን እውን በማድረግ ያችን ከትርምስ ጫፍ የነበረችን ሃገር እና ማጥ ውስጥ የነበረን ህዝብ ከማረጋጋትም አልፈው ወደ ዕድገትና ከፍታ ጎዳና መሯቸው፡፡
ኤምባሲው እንዳስታወቀው ለዚህ ውለታቸው ነበር እ.ኤ.አ በ 1997 ዓ.ም የአዛርባጃን ፓርላማ ሰኔ 15ን ብሄራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር የወሰነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *