ጥር 17,እሁድ ምሽት 4 ሰአት ,2012 ዓ.ም በጭጋጋማው አየር በራሱ የግል ሂሊኮፕተር ሲበር በደረሰ የመከስከስ አደጋ የሉስ አንጀለስ ሊከርስ ክለብ ኮከብ ተጫዋች ኮቢ ብራየንት በ41 አመቱ ሂወቱ ማለፉን ሲ ኤን ኤን በሰበር ዜናው አሰምቷል ።ከእሱ ጋር ሂሊኮፕተር ውስጥ የነበሩ የ13 አመት ልጁን ጨምሮ አራት ሰዎችም አብረው ከብራይንት ጋር ጋር ይህቺን አለም ተሰናብተዋል። ሂሊኮፕተሯ ካላብሳስ በተባለች የሉስ አንጀለስ አነሰተኛ ከተማ ላይ ነበር የተከሰከሰችው። ኮቢ ብራያንት ሁለት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ፣18 ግዜ ምርጥ የኤን ቢ ኤ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠ ሲሆን እኤአ 2008 እና 2012 ደግሞ የአሜሪካ ምርጡ ወንድ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ተብሎ ተመርጣል። ኮቢ ብራያንት ቬኒሳ ከተባለች ሚስቱ አራት ሴት ልጆች አፍርቷል።