የቀጨኔ መካነ መቃብር 45,000 የሚጠጉ አስከሬኖችን ወደ ቀረጢት ሊከት ነው

በ 111,479 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኘው የቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ በውስጡ ካሉት መቃብሮች ውስጥ 45,000 የሚጠጉ አስከሬኖች በቀረጢት በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው ትልቅ ፎቅ ውሰጥ የሚገኝ ሳጥን ውስጥ ሊከት ማቀዱን ለፊደል ፖስት ገልፇል።

ወደ ቀረጢት የሚገቡት አስከሬኖች ከተቀበሩ ሰባት አመት ያለፋቸው እንደሚሆኑ የዘላቂ ማረፊያው ስራ አስኪያጅ አቶ መኮንን ከስኬ ተናግረዋል።
” ለሟች ቤተሰቦች ምን አልባት ሰባት አመት ያለፈውን አስክሬን አውጥተው ሌላ ቦታ ማስቀበር የሚፈልጉ ከሆነ ማስታወቂያ ዘላቂ ማረፊያው መግቢያ በር ላይ ለጥፈናል “

” ወደ ቀረጢት የምንከትበት ምክንያት ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ወደ ፊት የሚቀበረውን ሰው ማስተናገድ ስለማንችል የግድ አፅማቸው የቀረ አስከሬኖችን አውጥተን ለአዲስ ቀብር ቦታ ማዘጋጀት ስላለብን ነው።” ብለዋል።
የቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ነገር ማድረጉን ሀላፊው አውስተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *