የሬጌ አቀንቃኟ ጃ9 ቅዳሜ በአዲስ አበባ በምታቀርበው ኮንስርት ጎን አልበሟን ትለቃለች


ጃማይካዊ የሬጌ አቀንቃኟ ጀኒን ኤልዛቤት ( ጃ9) በመጪው ቅዳሜ መጋቢት አምስት በቪላ ቨርዴ ሆቴል የሙዚቃ ኮንሰርት ስታቀርብ አንድ ቀን ቀድም ብሎ መጋቢት አራት ደግሞ “ዮጋ እና ከሬጌ ጋር “አስማምታ ወርክሾፕ በማርዮት ሆቴል ታቀርባለች።
የ36 አመቷ ጃ9 “Note to self ” የተባለው አዲስ አልበሟን በአዲስ አበባ ሆና በአለም ለሚገኙት አድናቂዏቿ ትለቃለች።
ዝግጅቱን ቬንቸር አዲስና ቲም ሉባንክ ከ ኩል ሆሊስቲክ ጋር ተቀናጅተው ሲያቀርቡት የፕሮግራሞቹ መግቢያ ትኬት በማርዮት ሆቴል እንደሚገኝ አዘጋጆቹ ለፊደል ፖስት ገልፀዋል።
ኮንስርቱ 300ብር ፣ ዮጋው ወርክሾፕ 250 ብር ሲሆን አልበሙ በ400 መቶ ብር እንደሚገኝ ተገልፇል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *