የመለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ የነበሩት ኢኮኖሚስቱ ነዋይ ገብረአብ ማን ናቸው?


መለስ ዜናዊ በአብዛኛው በእሱ ዘመን ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ( IMF) ,ከአለም ባንክ ለተበደረቻቸው ብድሮች ሽበታሙን መልከ መልካም ሰውዬን አቶ ነዋይን ገበረአብን ሳያማክር ያደረገው ነገር የለም ።ሲበዛ ያምናቸዋል ። ተው ይሄ ነገር ጣጣ ያመጣብሀል ካሉት ብዙ ግዜ መለስ አቅዱን ይተወው እንደነበረ ይነገራል ።

እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ ከአውሮፓ ህብረት ፣ከቻይና ፣ከእንግሊዝና ከሌሎች ከሀብታም ሀገራት የሚመጡ ብድሮች የነዋይን ጠረጴዛ ሳይነኩ አላለፉም ።ብድሮቹን አንደ ድርሰት መፅሀፍ አንብቦ ይገመግማቸው ነበር ።
ያደጉት ሀገራት ለሚያወጡት በካይ ጭስ ለአፍሪካ ካሰ መከፈል አለበት ብሎ መለስ ዜናዊ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር ከአቶ ነዋይ ጋር በጉዳዪ ላይ አውርቶበት እንዲሁም የመከራከርያ ሀሳብም ወሰዶ ነበር ።
መለስ የደርግን መንግሰት አስወግዶ ስልጣን ከያዘ በኋላ ።ከውጭ ለሚያገኛቸው ብድሮች የሚያማክረው ሰው ይፈልግ ነበር ። ነዋይ የሚባል ሰው አለ ። ሀይለ ስላሴ የዪቨርስቲ ( አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ) በኢኮኖሚክስ ተመርቋል ።በንጉሱ ግዜ ልማት ባንክ ሰርቷል ። ።ውጪም ትምህርት የቀመሰ ነው ።በብሪቴንም የአማካሪነት ስራ ሰርቷል ተብሎ ተነገረው መለስ እስቲ ልየው ብሎ ነዋይን አስጠራው ። ነዋይም ከውጭ እርዳታና ብድር በኩል ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ሲያወራ መለስን ማረከው ። በውጭ ሀገር ኖሮ በ991 ሀገሩ ጠቅልሎ የገባው ነዋይ በ1987 ዓ.ምም የኢትዮጵያን ብድሮች ላይ እንዲመከር አማካሪ ሆነ ተሾመ ። ኢትዮጵያ በበድር ለሰራቻቸው መንገዶቸ ፣ጤና ጣቢያዎች ፣ሆስፒታሎች ፣ባቡር ሀዲዶችና ሀይል ማመንጫ ግድቦች የነዋይ ምክረ ሀሳቦች ነበረባቸው።

በአቶ በነዋይ ላይ ሁለት ተቃራኒ ሀሳቦች ይነሳሉ። አንደኛው ሰውዬው ኢኮኖሚክስን የተረዳ የሚገኙ ብድሮች የመንግስት የልማት ፓሊሲ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳያመጡ ቀድሞ የሚረዳ ሰው ነው በማለት ሲያወድሱት እንዳንዶቹ የሚገኙ ብድሮች በቅጡ ስራ ላይ ሳይውሉ በሙስና እየተበሉ ሀገሪቱ የውጭ እዳ ስታስግበሰብስ ዝም ብሎ ያየ ፣ሀገሩቱ እዳ ቢቢልየኖች ዶላር ሲከማች ፣የዋጋ ንረቱ ከ20% በላይ ሲሆን የረባ ሀሳብ አላመነጨም እንደውም እዳ የዘፈቀን አማካሪ ነው ብለው ነዋይን ይኮንኑታል።
መለስ 2004 ዓም ነሀሴ ላይ ከሞተ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ሰውዬውን በ2008 ዓም በጡረታ አሰናበቷቸው ። መሰናበታቸው በገዛ ፍቃዳቸው ነው ቢባልም ከፍተኛ የውጭ ብድር እና ስራ አጥነት ራስ ምታት የሆነበት ሀይለማርያም በሰውዬው አማካሪነት ብዙም ስላልተማረከ ነው ተብሎም ተፈርጆ ነበር ። ከዛ በኋላ፣ሰውዬው የኢትዮጰያ ልማት ኢንስትትዩትን ቢመሩም እምብዛም ሳይቆዪ ስራውን አቁመውታል።
አቶ ነዋይ ኢትዮጵያ እና ጃፓን በልማት ትስስር ዙርያ በስድስት ወር አንዴ የምክክር መድረክ እንዲኖራቸው በማድረግ ላለፉት አስር አመት ለፍተዋል ።
የጃፓን መንግስትም የካይዘን ፍልስፍና ኢትዮጵያ እንድትሰራበት ስላስተዋወቁ ” Order of the Rising Sun ” በሚል ሂልተን ሆቴል በተደረገ የምሳ ግብዣ ላይ አቶ ነዋይን መሸለሙ ይታወሳል።
በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የኢትዮጰያ ፓሊሲ ላይም ላቅ ያለ ተሳትፎ ነበራቸው ። ከዚህም ባሻገር ወርክ ሾፕ ላይ ተጋብዘው ጥናት ሲያቀርቡም ሆነ ሲናገሩ ያስደምማሉ ።ሰውን ያዳምጣሉ ። ውስብስብ የኢኮኖሚ ሀሳቦችን ሲያስረዱ ሰዎች በሚገባቸው መንገድ ነው ተብለው ይሞገሳሉ።
ኢኮኖሚስቱ ዶክተር ተኬ አለሙ ስለነዋይ እንዲህ ሲል ለፊደል ፓስት ተናግሯል ” ነዋይ ኢኮኖሚክስ የገባው ነው ።ኢኮኖሚክስን ከቲዎሪ ጋር ብቻ ሳይሆን ከነባር ሁኔታ ጋር የሚያስረዳ ነው ።በተሳተፋባቸው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ሀሳቡን ቀለለ ባለና በሚያሳምን መንገድ ያስረዳል ።”
በ80 ዎቹ እድሜ መጀመርያ እድሜ የነበሩት እና ከላፉት ሁለት አመታት ጀምሮ ከእርጅና ጋር በታያዘ ድካም ይታይባቸው የነበሩትና ዛሬ የካቲት 16,2012 ጠዋት አራት ሰአት ገደማ ህክምና ከሚከታተሉበት አዲስ አበባ በሚገኘው ኖርዲክ ያረፉት አቶ ነዋይ በዶክትሬት ዲግሪ ባይመረቁም ከኦክስ ፎርድ ዪንቨርስቲ ያገኙት የሊት ኦኮኖሚክስ ዲግሪ በአንዳንድ ሀገራት ከዶክትሬት ትምህርት ጋር የሚስተካከል ነው ።

አቶ ንዋይ ከሶስት ዓመት ዓመት በፊት የአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነር ለመሆን የኢትዮጵያ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ቢቀርቡም በመጨረሻው ዙር በካሜሩን እጩዋ ቬራ ሶንግዊ ተሸንፈው ፕሬዝዳንት ሳይሆኑ ቀርተዋል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *