ካፒታል ሆቴል ልክ እንደ ሼባ ማየልስ ለደንበኞቼ ሽልማት አዘጋጅቻለው አለ



ከሰባት አመት በፊት የተከፈተው ባለ አምስት ኮከቡ ሆቴል ካፒታል ሆቴል እና ስፓ እኔ ጋር መኝታ ፣ምግብ እና ጂም ለሚሰሩ ደንበኞቼ ልክ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በእያንዳንዱ በረራ ተጓዦችን የሼባ ማየልስ ካርድ ሰጥቶና ነጥብ ሰብስስቦ በተጓዙት ኪሎ ሜትር የነፃ ትኬት እንደሚሰጠው ሁሉ ሆቴሉን ተመላልሰው የተለያዩ ነገሮችን ለሚጠቀሙ ደንበኞች ሽልማት አዘጋጅቻለው ብሏል።
ካፒታል ሆቴል ማኔጅመንት ትናንት ሀሙስ ለደንበኞቹን እራት ግብዣ አድርጎ የሽልማት ፕሮግራሙን አስጀምሯል።
የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ባንታየው ወልደሚካኤል ለፊደል ፓስት እንደተናገሩት ደንበኞች ሞባይላቸው ላይ ለሽልማቱ የተዘጋጀውን አፕልኬሽን በመጫን ከ100 ብር ጀምሮ ለሚጠቀሙት ነገር በማስመስዝገብ ነጥብ እየሰበሰቡ የሽልማቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ብለዋል ።
ሸልማቱ በነፃ የሆቴሉን አገልግሎቶች ከማግኘት ጀምሮ የተለያዩ ስጦታዋች ተካተውበታል።
ካፒታል ሆቴል ከ400 በላይ ሰራተኞች አሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *