በድርቅና በግንደ ቆርቁር ምክንያት በአማካኝ በአመታዊ በበቆሎ ምርቷ ላይ እሰከ 30 ፐርሰንት ጉዳት የሚያደርስባትን ኢትዮጵያን ለመርዳት የባለፀጋው ቢል ጌት ድርጅት ከሆነው ሞንሳንቶ በነፃ ተገዝቶ ለሙከራ በመልካሳ እና በባኮ የግብርና ማእከል የተተከለው ሞኔቶ A8 10 የተባለው በዘረ መል ምህንድስና የተፈበረከው በቆሎ መልካም ውጤት አያሳየ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ገለፀ።
የዘረ መሉ በቆሎን ግንደ ቆርቁሮቹ መጥተው ቅጠሉን ሲቀምሱት ለሆዳቸው ስለማይሳማማቸው በቆሎው በነሱ ሳይበላ ማደግ እንደቻለ ለሁለተኛ ጊዜ 144 ሚትር ስኴር ላይ በተተከለው የመልካሳ ግብርና ምርምር ውጤት ማወቅ እንደተቻለ ተነግሯል።
በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የበቆሎ ማሳቸው በግንደ ቆርቁር እንዳይበላ በአመት እስከ 10,000 ብር ድረስ ለተባይ ማጥፊያ መድሀኒት የሚያወጡ ሲሆን ይሄ የዘር መል በቆሎ ተከታታይ ሙከራዎችን አልፎ ለገበያ ከቀረበ ከወጪ ይታደጋቸዋል ተብሏል።
ኢትዮጵያ በአንድ ሄክታር በአማካኝ አስከ 40 ኩንታል በቆሎ ስታገኝ ሙከራ ላይ ያለው በቆሎ ከ70 አስከ 80 ኩንታል በአንድ ሄክታር እያሰገኘ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ትናንት ቅዳሜ የመልካሳን ግብርና ማእከል ለጋዜጠኞች ባስገኞበት ወቅት ገልፇል።
” በግብርና ማእከሉ ላይ ጥሩ ውጤት አስገኘ ማለት አይደለም አርግጠኛ ለመሆን ተከታታይ ሙከራዎች ያስፈልጋሉ።ከዛም ከአካባቢ ብክለት ፣ከሰው ከጤና፣የበቆሎ ቅጠሉም ለከብቶች ምግብነት ስለሚውል ጉዳት ማምጣቱና አለማምጣቱ ተመዝኖ ነው ለገበያ ሊቀርብ የሚችለው” ሲሉ የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ታደሰ ዳባ የገለፁት።
በሙከራ ላይ ያለው የበቆሎ ዘር ገበያ ላይ የሚቀርብ ከሆነ በአንድ የዘር አቅራቢ ሳይሆን በብዙ ሀገር ውስጥ ባሉ የዘር አቅራቢዎች ለገበሬው እንደሚከፋፈልም ታውቋል።
ኢትዮጵያ አመታዊ የበቆሎ ምርቷ 87 ሚልየን ኩንተል ሲሆን ከ70 በላይ የበቆሎ ዝርያዎችም በገበሬው ማሳ ላይ ተተክለው ይገኛሉ።
አስከ አሁን በዘረ መል ምህንድስና ማሳ ላይ እንዲበቀል የተፈቀደለት ዘር ጥጥ ቢሆንም ከዘሩ የዋጋ ውድነት የተነሳ ገበሬዎች እየተጠቀሙበት አይደለም።