።
ፊደል ፖስት ከታማኝ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት ከነገ መጋቢት 9,2012 ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ ሰርጭት ስጋት ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሱዳን ( ካርቱም) ፣ግብፅ ( ካይሮ) ሊባኖስ ( ቤሩት) ፈረንሳይ ( ፓሪስ) ኬንያ( ናይሮቢ እና ሞምባሳ ) ኳታር ( ዶሀ) የሚያደርገውን በረራ ላልተወሰነ ጊዜ ሰርዟል።
የዱባይንና የሌሎች ሀገራትንም በረራ ሊሰርዝ ይችላል የሚል መረጃ ፊደል ፓስት ደርሶታል ።
አየር መንገዱ በቀን ካርቱም (3) ካይሮ(1) ፣ቤሩት (1)፣ፓሪስ(1) ናይሮቢ (3) እና ዶሀ (3) በቀን በረራ ያደርግ ነበር ።
ኢትዮጵያ ውስጥ አስከ አሁን ስድስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ይታወቃል።
ፊደል ፓስት በቀደመው መረጃ እንዳስታወቀውየኮሮና ቫይረስ የጠቅላላ የጉዞ በረራውን ከ20 ፐርሰንት በላይ የቀነሰበት 16,000 ገደማ ሰራተኛ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞቹ ከሳምንት በፊት በላከው የኤሜይል መልእክት በአየር መንገዱ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቢሮዎችን አሁን ካለው ገበያ አንፃር አይተው አላስፈላጊ የተባሉ ቢሮዎችን እና ሰራተኞችን እንዲቀንሱ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ሰራተኞቹ ያልተጠቀሙበት የቫኬሽን ጉዞ ካለ ቶሎ እንዲጠቀሙበትም አሳስቧል።
በተጨማሪም ከአየር መንገዱ የሚሰሩ ኤርፓርቶች፣ምግብና መጠጥ አቅራቢዎች፣ ሆቴሎች ጠበቆች፣የነዳጅ አቅራቢዎችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች የዋጋ ቅናሽ እና አንዲያደርጉና ለጊዜው ውል እንዲያቋርጡ ጉዳዩን ለሚመሩት የአየር መንገድ ክፍል ሀላፊዎች አሳስቧል።