ኡጋንዳዊው አንጋፋው ተቃዊሚ መሪ ለ 51 ግዜ ታስረዋል።

የፎረም ኦፍ ዴሞክራቲክ ቼንጅ መሪው ዶክተር ኪዛ ቢስግዊ ባለፈው ሰኞ በጂንጃ ከተማ ውስጥ ቦስግዋ የተባለ ኤፍ ኤም ጣቢያ ላይ ቶክ ሾው ፕሮግራም ለመሳተፍ በሚያቀኑበት ወቅት በመንግስት ፓሊሶች መታሰራቸውን የተለያዪ የኡጋንዳ ሚድያዎች ዘግበዋል። የ63 አመቱ ዶ/ር ኪዛ ብዙ ጊዜ በመታሰር የአለም ጊነስ ቡክ ላይ በሰፈሩ ማግስት ነው የታሰሩት። ብዙ ግዜ በንግግራቸው አመፅ ያነሳሳሉ በመባል በፓሊስ የሚታሰሩትና ከቀናቶች በኋላ የሚፈቱት ዲ/ር ኪዛ “እስር ቤት ለምጄዋለው ቤቴ ነው ሲሉ” ይደመጣሉ።ሰውየው በተደጋጋሚ ለፕሬዝዳንትነት ቢወዳደሩም ለ33 አመት ኡጋንዳን የመሯትና አሁንም በስልጣን ላይ ያሉትን ዪወሪ መሴቬኒን ማሸነፍ አልቻሉም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *