አፍሪካዊቷ ማዳጋስካር ለኮሮናቫይረስ ባህላዊ መድሀኒት አግኝቻለው ብላለች


ቲቪ ኤም በተባለ የብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ዛሬ ቀርበው ንግግር ያደረጉት የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና ሀገራቸው በኮሮናቫይረስ የተያዘን ሰው የሚያሽል አንዲሁም እንዲያዝ የማያደርግ ባህላዊ መድሀኒት እንዳገኘች ተናግረዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ ከሆነ መድሀኒቱ የተፈበረከው በማዳጋስካር እኒስቲትዮት ኦፍ አፕላይድ ሪሰርች በተባለ የምርምር ተቋም ሲሆን ” ዎርምውድን ጨምሮ ሌሎች ቅጠላቅጠሎችን መድሃኒቱን ለመስራት ተጠቅመናል በቅርቡም መድሀኒቱ በስፋት ለገበያ ይቀርባል “ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *