አኩርፋለች

አኩርፋለች

#ሰላም#EFDA#FIDEL

ተጫዋች ናት ።እለት እለት ፊቷ በፈገግታ የተሞላ፤ ኩርፊያ ብሎ ነገር የማታውቅ
ደግ፤ ሩህሩህ፤ልበ ቀና ነች
ቤታችን ልክ እንደቤቷ ነው
ማጀቱ ፤ሌማቱ፤ ግቢው የኛ የሆነው ሁሉ የእሷም ነው
እለት እለት እኩለ ቀን የእሷ ወደ ቤታችን መምጣት ልክ ምሳ አቅርቦ እንደመብላት ነው
ሳቁዋ ብቻ አይደለም ቁጣዋም ይናፈቃል
የቤታችን፤ የግቢው፤የሰፈሩ ሁሉ ድምቀት ናት
ሰአቱ ደረሰ. . . .ቤቱ እሷን ናፍቋል
ጣ ጣ ጣ . . .ሠከንድ ይፈጥናል ደቂቃም ቢሆን ሳይዘገይ ይከተለዋል 1 ሠዐት ነጎደ
ቀርታለች . . . ምን ገጥሟት ይሆን ሃሳብ ገባኝ
ግዜ ሣላጠፋ ከቤቷ ደረስኩ
በራፉዋ ላይ ተቀምጣ ትክዝዝዝዝዘ ብላለች
ገና ስታየኝ ፊቷን በነጠላዋ ከልላ አንገቷን ጥምምዝዝ አደረገች
አንድ ነገር እንዳለ ገባኝ ምን ይሆን….
ብዙ ልታወራ ፍቃደኛ አይደለችም
እንደምንም ላግባባት ሞከርኩ
የዋህነቷ ገፍቷት አይኗ እንባ እያቀረረ ትላንት ማታ በጨዋታ መሃል የዘላበድኩት ነገር ልቧን እንደሰበረው ሳትደብቅ ነገረችኝ
ደነገጥኩ !!! እንዴት አይነት ስህተት እንደሰራሁ አሰብኩ
ፀፀተኝ
እሷስ ጥሩ ልብ አላት ፣ ቂም በቀል አታውቅም፤ በይቅርታ ታምናለች
ግን ስንቶቻችን እንሆን በጨዋታ መሃል አሊያም ረብ በሌለው ክርክር
የወዳጆቻችንን አይነኬ ድንበር ጥሠን ያልተገባ ፀብ ውስጥ የምንገባው፤ ወዳጆቻችንን የምናስከፋው
እኔ የሌሎች መማሪያ ነኝ !
እኔም ሆንኩ ሌሎች ንግግራችን፤ ስራችን፤ አካሄዳችን ፤ውሎአችን ሁሉ
ሌሎችን የማይጋፋ፤ ስብዕናቸውን ያከበረ ፤ መልካምነታቸውን የማይበርዝ መሆን እንዳለበት ገብቶኛል
ራሴን አርሜአለሁ ተግበባብተናል!
ቶሎ ወደ ራሤ መመለሤ የእሷን ፍቅር መልሶ ሠጥቶኛል
ይህ ውሳኔዬ ለልቤ ንፅህና ፤ለአይምሮዬ ነፃነት ሰጥቶታል
ይህንን በረከት ለሌሎች ማካፈል እፈልጋለሁ
በይቅርታ እንመን፤በፍቅር እናውራ፤ በመግባባት እንጓዝ፤ በመሃላችን ሰላም ይስፈን!!
ትምህርት ለልማት ማህበር ወጣቶችን ወደ ሰላም አውድ ለማምጣት የሚሰራ ሃገር በቀል ድርጅት ነው ፡፡የመንግስት ሃላፊዎችን ከወጣቶች ጋር በማቀራረብ የማወያየት ስራን እየሰራ ነው ፡፡ በወለጋ ጊምቢ፣ነጆ እና ቅልጡ ካራ ወረዳዎችም ላይ ከ120 በላይ ወጣቶችን እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ስለሰላም አወያይቷል ፡፡ ተሳታፊዎች ተቀራርበው እንዲሰሩ ድልድይ ሁኗል፡፡
ስለ ሰላም መስበክ ፣ስለሰላም መዘመር ፣ ለሰላም ዘብ መቆም የሁላችን የቤት ስራ ነውና ሁላችን እጅ በእጅ ተያይዘን ስለ ሰላም እንቁም ፣ ሰላም ለሁላችን ፣ሰላም ለሃገራችን ይሁን !!!!
ይህ መልዕክት የተላለፈላችሁ በትምህርት ለልማት ማህበር (Education For Development Association) ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *