አንጀሊና ጆሊን ጨምሮ በወሲብ ጥቃት የሴቶች እንባ ያለበት ዊይንስተን ለ23 አመት ወህኒ ወርዷል
ታሪኩ እንዲህ ይጀምራል ።ተነባባው ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ ከሶስት አመት በፊት በታዋቂው የፊልም ፕሮዲውሰር ፣የሚርማክስ የፊልም ፕሮዳክሽን ባለቤት፣ በ67 አመቱ ሀርቪ ዊይንሰተን ፈፅሞታል በተባለው ከሴቶች ይደርሱት የነበሩትን የወሲብ ትንኮሳና ጥቃት ፅፎ ማተም ጀመረ ። ከፅሁፎቹ መሀከል ተዋናዮቹ ሮዚ ማክግዋንና እና አሽሊ ጁዲ ታሪኮች ሲገኙበት ዊይንስተን አስገድዶ ወሲብ ከመፈፀሙ ባሻገር ሴቶችን እራቁቱን እንዲያዩትና ሰውነቱን” ማሳጅ አድርጉኝ” በማለት እንደማባባያም” ፊልም ላይ እንዲትተውኑ አደርጋችለው ፣የተሻለም ስራ አሰጣቸዋለው” ይል ነበር ሲል ፅሁፎ ተጠቂዎችን በማናገር ፅፏል።
ከፅሁፉ በኋላ የጋዜጣውን ፖስታ ፣ኢሜይል ተጨናነቁ።እኔንም ደፍሮኛል የሚሉ ውንጀላዎች በዙ። ከሱ ጋር ሰርተው ከነበሩት መሀል እቤቱ ፣ሆቴል ።ቤሮ ውስጥ ሳንፈልግ ዊይንስተን የወሲብ ጥቃት ፈፅሞብናል የሚሉ ውንጀላዎች ተበራከቱ።

የ44 አመቷ ተዋናይ አንጀሊና ጆሊ በወጣትነቷ ከዊይንስተን ጋር የነበራት የስራ ግንኙነት ” መጥፎ የስራ ጊዜ ” ብላ ስትጠቅስ ዊይንሰተን ባዘጋጀው “ሺክስፔር ኢን ላቭ” ፊልም ላይ የተወነችው ጃኒት ፓልትሮ ደግሞ በተደጋጋሚ የወሲብ ጥያቄ ያቀርብላት እንደነበር ተናግራለች ።
የዊይንስተን ረዳት ሆና ስተሰራ የነበረችው ዜንዳ ፔልስኪን ደግሞ “ማሳጅ እንዳደርገው ጠይቆኝ ከዛ ወደመኝታ ቤት ለመውሰድ ጎተተኝ ፣ይሄን ጉዱን አወጣለው ስል 125 ሺ ፓውንድ ማባበያ ከፈለኝ” ብላ ተናግራለች ።
ዊይንሰተን ውንጀላው ሲበዛበት የራሱ ፈልም ፕሮዳክሽን ካምፓኒ ከስራ አሰነባተው ። ከብሪታኒያ የፊልም እና የቴሌቭዥን አካዳሚም ታገደ ።ሞሽን የስእልና ጥበብና ሳይንስ አካዳሚም እንዳትደርስብን አሉት ። ሁለት ልጅ የወለደችለት ሚሰቱ ጂዮርጂና ቻፕማን ከሰውዬው ጋር ያላት ትዳር ማብቃቱን ተናገረች።” አዝናለው ።ቅስሜ ነው የተሰበረው ” በማለት በቧሏ የወሲብ ጥቃት ድርጊቶች እንዳዘነች ተናግራለች።
በዋሽንግተን ፣በኒውዮርክ እና በሎንዶን ያሉ ፖሊሶች የአምስት ልጆች አባት በሆነው ሰውዬው ላይ ምርመራ ጀመሩበት ።
የኒዮርክ ታይምሱ ጋዜጠኛ ሮናን ፋሮው ዊይንሰተን ሌላ ጉዱ በጋዜጣ እንዳይወጣበት የብሪቲሽና እስራኤል የሆነ “ብላክ ከብ” የተባለ ሰላይ ቡድን ቀጥሮ እሱን ስሙን የሚያጠፉትን ሰዎች ሀሰተኛ የወሲብ ታሪክ በመፈብረክ ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨ መሆኑን ፃፈ ። በተለይ አስገድዶ ደፍሮኛል ብላ በቲዊተር ገፇ የፃፈችውን ተዋናይ ሮዚ ማክግዋን ስሟን ለማጠልሸት ዊይንሰተን በቀጠረው የስለላ ቡድንና በጋዜጠኞች በኩል ስሟን አጥፍቶታል ሲል ፋሮው ተናገረ። ማክግዋን” አንድ ሚልየን ዶላር ልክፈልሽና ያደረኩብሽን “ነገር አትናገሪ ሲል ዊይንስተን እንደጠየቃትና እሷም እምቢ እንዳለች ተናገረች።
ነገሮቹ ከረሩ ።በአሜሪካ  #MeToo hashtag ወይንም “እኔም ” የሚል ሰዎች በአለቆቻቸው ወይንም በሌሎች ሰዎች የደረሰባቸውን ወሲባዊ ጥቃትና በደል በማህበራዊ በሚድያ ግሩፕ በመፍጠር በማውራት ጉዳዩ ትልቅ አጀንዳ አገኘ ። ይህ እንቅስቃሴ ከአሜሪካም ያለፈ በሌሎችም ሀገር እንቅስቃሴ ነበረው።
በ2010 ዓ.ም ሶስት ሴቶችን በተለያየ ቦታና ግዜ ደፍሯናል በማለታቸው ለቀረበበት ክስ በአንድ ሚልየን ዶላር ዋስ ከእስር ተለቆ የነበረ ሲሆን ሲንቀሳቀስ የት እንዳለ የሚያሳይ መሳርያ ጉልበቱ ላይ ገጥሞ እንዲሄድም ታዞ ነበር ።ብዙ ተግባራዊ ባያደርገውም።
በ2011ዓ.ም ዊይንሰተን ወሲባዊ ጥቃት አድርሶብናል የሚሉ ወንጃዮችን ቃለመጠየቅ በማድረግ ” አይነኬው” ወይንም “Untouchable “የሚል ርእስ ያለው ዶክመንተሪ ፊልም በዊይንሰተን ላይ ተሰራ።

አሽሊ ጁዲ የወሲብ ጥያቄ አቅርቦልኝ ስላልተቀበልኩት ብዙ ስራዎቼን አበላሽቶብኛል ብላ ከሰሰች። ፍርድ ግን አላገኘችም ።በፓላንድና በካናዳ አስገድዶ ደፍሮናል የሚሉ ክሶች ቢመጡም ሰዉዬውን አስር ቤት አላስገቡትም። የቅርብ ረዳቱ የነበረችው ሮውና ችው አስገድዶ መድፈር ሙከራ እንዳረጋባት ተናግራ እራሷን ከወሲብ ጥቃት ለመከለሰከል ስትል ከዊይንሰተን ጋር ለስራ ስትንቀሳቀስ ሀለት የሱሪ ታይቶችን ደርባ እንደምታደርግም ገልፃ ነበር።
ነገር ግን ከ14 አመት በፊት የፊልም ፕሮዳክሽን ተባባሪ ሆና ከእሱ ጋር ስትሰራ የነበረውን ሚሚ ሀሊን የኦራል ሴክስ በግዳጅ ፈፅሞባታል በሚል ክስ እና እንዲሁም የቀድሞ ተዋናዯን ጂሲካ ማንን ከሰባት አመት በፊት አስገድዶ ደፍሯል ተብሎ በቀረበበት ክስ ዳኛው ጄምስ በርክ ትናንት እሮብ መጋቢት ሁለት የ23 አመት አስር ፈርደውበታል።
ፈርዱ ከመወሰኑ በፉት በጀርባ ህመም ሆስፒታል የነበረው ዊይንሰተን ” ይሄ በአሜሪካ ምድር እንዴት ይሆናል! እኔ ጨዋ ነኝ ።በማለት ለቅሶ በታከለበት ድምፅ ተቃውሞውን አሰምቷል።
የጀርባ ህመም ስላለበት በእጅ መደገፊያ ወደ ፍርድ ቤት የገባው ከመቶ በላይ ሴቶች ደፍሮናል ብለው ውንጀላ ያቀረቡበት” የሼክ ስፔር ኢን ላቭ “ፊልም ፕሮዲውሰር ሀርቪ ዊይንሰተን አንዲህ ብሏል” ግዴ የለም የተሻለ ሰው ሆኘ አሰርቤቱን እወጣበታለው።ምን አልባት ልጆቼን ዳግም ላላይ ብችልም ” ሲል ተደምጧል።

በማንሀታን ፍርዱ ከተሰማ በኋላ ከነበረበት ወንበር ያልተንቀሳቀሰው ዊይንሰተን እጁ ላይ ካቴና ተጠልቆለት በብሉቨር ሆስፒታል ደም ግፊቱን ከታየ በኋላ ወደ ሚያርፍበት የኒዎርኩ አይላንድ ሪከር እስር ቤት አምርቷል።
ጠበቃው ሩኖቶ ግን” ደፈረን ያሉ ሴቶች ሁላ በፍቃዳቸው ነው ከደንበኛዬ ጋር ወሲብ የፈፀሙት በማለት ” የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቃውሟል።

እግዚአብሄር ጤና ካደለው የ67 አመቱ ዊይንስተን በ90 አመቱ ከአስር ቤት ይወጣል ማለት ነው።
ዊይንሰተን ሁለት የወሲብ ክሶቹ የተቋረጡለት ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝባቸው ኖሮ እድሜ ልክ ያሳስሩት ነበር ።

ከሳሽ ሀይሊ ከፍርዱ በኋላ እንዲህ አለች ” ያኔ ምሽት ሲደፍረኝ ።መብቴን ነወ የተገፋኝ ።ሰውም እንዳላምን ነው ያረገኝ ።በራስ መተማኔን ጠፍቶ ነበር ። ዊይንስተን የሚገባውን አግኝቷል ።ከህግ በላይ እንዳልሆነም ዛሬ ተረድቷል።” ብላለች ።
ጂሲካ ማን ደግሞ እንዲህ አለች ” እኔ ላይ የደረሰውን ጥቃት ማዳን ይቻል ነበር ። ከእኔ አድሜ በጣም በሚበልጥ ሰው መደፈር ያማል ። የደረሰበኝ ነገር አስክሞት ከእኔ ገር ይኖራል ።የሱ ጠበቆች እውነትን አጣመዋት ነበር ። ከእስርቤቱ አጥር ውስጥ ዊይንሰተን ከአይምሮው በሽታው ያገግማል።ጥፋተኛ በሆነበት ወንጀል እስር ቤት መግባቱም ፍትህ ቢዘገይም ቀን ጠብቆ ይመጣል ልል አስችሎኛል ” ብላለች።
ከዊይንሰተን ፍርድ በኋላ በሰውዬው ጥቃት ደረሰብን የሚሉ ሴቶችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቀኑን በማህበራዊ ድህረ ገፆቻቸው ልዪ ቀን በማለት ሲያሞግሱት ተስተውሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *