ቴዲ አፍሮ ለቅዳሜው ኮንሰርት የተከፈለው ብር ምን ያክል ነው?

መስቀል አደባበይ ቅዳሜ የካቲት 14 ምሽት ላይ በነበረው ኮንሰርት ላይ ምን ያክል ሰው ታደመ? ምን ያክል ብርስ ገቢ ተገኘ? ምን ያክል ብር ለቴድሮስ ካሳሁን ተከፈለ የሚለውን ጥያቄ መልስ ለማግኘት የቴዲ ማናጀር ጌታቸው ማንጉዳይ ጋር ፊደል ፓስት በስልክ ጠይቆ ነበር ። እንዲህም አለ “ፕሮግራሙ በሰላም ተጠናቆ ፤ የፍቅር ጉዞንም ኮንሰርት አምሮና ደምቆ በመካሄዱ ደስተኛ ነን። ምን ያክል ሰው እንደገባ ገና ተመላሽ ትኬት አጣርተን ትክክለኛውን ቁጥር እንናገራለን ።
ምን ያክልስ ብር ለቴዲ ተከፈለው?

ጌታቸው ” እንደዚህ አይነት ሒሳብ ውስጥ አንገባም። ዋናው ነገር ፕሮግራሙ ግቡን መምታቱ ነው ።

የፕሮግራሙ አዘጋጅ ላየንስ ፕሮሞሽን ይሄን ምላሽ ሰጥተዋል ።
“ቴዲ የተከፈለውን ብር እራሱ ይግለፅ እንጂ እኛ እንዲህ ነው አንልም። እሱ ሳይናገር እኛ ቀድመን ብንናገር መብት መጋፋት ይሆንብናል። ምን ያክል ሰው አንደገባ ደግሞ ለማወቅ ትኬቶቹ በዳሽን ባንክ በኩል ስለተሸጡ የነሱን ሪፓርት እየጠበቅን እንገኛለን ።
ለመድረክ ዝግጅቱ 83 ሰዎች እንደተካፈሉ የተወሰኑ የሙዚቃ መሳሪያዎችም ከጀርመን፣ ከአሜሪካና ከካናዳ እንደመጡና በአጠቃላይ ኮንሰርቱ ላይ የነበሩት የሙዚቃ መሳርያዎች ዋጋ 20 ሚልየን ብር እንደሚገመት እንዲሁም ለኮንሰርቱ የላይት አቃዎች ደግሞ 600,000 ብር እንደወጣ የመድረኩ አዘጋጅ ዊ ዶኮር ለፊደል ፓስት ተናገረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *