በደቡብ አፍሪካ የምትኖረው ራንዲካ ንሆንያማ በኤሌክትሪካል ኢንጀነሪንግ ዲፕሎማ ለመመረቅ 16 አመት የፈጀባት ሲሆን ሰሞኑን ሳትሰለች ትምህርቷን የተከታተለችበት ተሽዋኔ የቴክኒክ ዪንቨርስቲ በፌስ ቡክ ገፁ እንዳስታወቀው ” እድሜ ቁጥር ነው። ለመማር ፍላጎት ካለ በየትኛውም እድሜ መማር ይቻላል ።ለዚህ አንዷ ምስክር ደግሞ ራንዲካ ንሆንያማ ናት።በ43 አመቷ ሀይስኩል ገባች ከዛም ነርሲንግ ለመማር ብዙ ቦታ አመለከተች ግን መግቢያ ፈተናውን ማለፍ አልቻለችም።እኘ ጋር መጣች ብዙ ግዜ ወደቀች በመጨረሻ ግን ህልሟን አሳካች በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ በዲፕሎም ተመረቀች ” በማለት ዮንቨርስቲው ፅፏል።