የኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ዛሬ የካቲት 14 ለቀድሞው ጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የምስጋናና የሽኝት የእራት ፕሮግራም በስካይ ላይት ሆቴል ያዘጋጀ ሲሆን በስማቸውም ስራ ለመፍጠር ለሚፈለጉ ሀኪሞች እንዲሆን አንድ ሚልየን ብር ለስራ ፈጠራ ኮሚሽን እንደሚሰጥ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ዶክተር ማርቆስ ፈለቀ ለፊደል ፓሰት ተናግረዋል።
” ዶክተር አሚንን በአንተ ስም ፌዴሬሽኑ አንድ ነገር ማድረግ ይፈልጋል ብለን አማከርነው ።ከራሱ ጋር ከተማከረ በኋላ ብሩን ተመርቀው ስራ ካጡ የህክምና ተመራቂዎች መሀል ለክልኒክ መክፈቻ በተወሰነ መልኩ ድጋፍ እንዲሆን ሀሳባቸውን አወዳድራቹ ለአንዳቸው ስጧቸው” ብሎናል ሲሉ ተናግረል።
ዶክተር ማርቆስ አክለው ” እውነቱን ለመናገር ስራ መፍጠር ከሚፈልገው ሀኪም መሀል አንድ ሚልየን ብር ድጋፍ ኢምንት ናት ።ዋናው ሀሳብ ግን ሎሎችም ድርጅቶች ወይንም ግለሰቦች ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ለማነሳሳትና መነሻ ካፒታል የሌላቸው ብዙ የህክምና ተመራቂዎች የህክምና አገልግሎት መስጫ ከፍተው ማህበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ እራሳቸውንም እንዲጠቅሙ ነው በዶክተር አሚር ስም የተሰጠው ድጋፍ በጎ አስተዋፆ ያደርጋል” ብለዋል።
ዶ/ር አሚር አማን በአሁኑ ሰአት በአሜሪካዊው ባለሀብት ዋረን ቡፌት ከ56 አመት በፊት የተመሰረተውና በሴቶች ወሊድና ፅንስ ክትትል አለም ላይ ያለትርፍ በሚሰራው ሱዛን ቶምፕሰን ቡፌት ፋውንዴሽን በተባለ ተቋም ከፍተኛ አማካሪ ሆነው አየሰሩ ይገኛሉ።