በኦሮሚያ ታርጋ ለመቀየር እሰከ 10,000 ብር ድረስ ጉቦ አየተጠየቀ ነው



ሰሞኑን በኮድ 3 ዶልፊን ፣ዳማስ እና D4D መኪኖችን በህዝብ አገልግሎት ስም ገብተው የግል ስራ አየሰሩ ነው የተባሉትና ታርጋቸውን ወደ ኮድ 3 አልያም ኮድ አንድ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በጉሙሩክ ኮሚሽን እንዲቀይሩ የታዘዙት ባለንብረቶች ታርጋችንን ለመቀየር ብር ድረስ በኦሮሚያ ትራነስፓርት ሰራተኞችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች በኩል ጉቦ አስከ 10,000 ብር ድረስ ጉቦ እየተጠየቅን ነው ሲሉ ለፊደል ፓስት ተናገሩ።
ከባለንብረቶች መሀከል ኢሳያስ ሀይሉ የተባለ ግለሰብ በቡራዩ ትራንስፓርት ቢሮ ተመልክቻለው ያለውን እንዲህ ተናግሯል ” ታርጋ ቀይሩልኝ ብለክ ማመልከቻ ስታስገባ ታርጋ አልቋል ቆይ ጠብቅ ይሉካል ።ጉዳይ አስፈፃሚ ነኝ የሚሉ ሰዎች ግን ብር ከከፈልክ ጉዳይክ ያልቅልካል ይሉካል ። ሰውም መጉላላት ስለማይፈልግ ይሄን እያረገ ነው ።ከ 2,000 አሰከ 10,000 ብር ደረስም ይጠይቁካል።” ብሏል።
በሰበታ፣በሱልልታ፣በቃሊቲ እና በለገጣፎም ታርጋ እያወጡ ያሉ ባለንብረቶች ተመሳሳይ ነገር እየገጠማቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ ፊደል ፓስት የኦሮሚያ ትራንስፓርት ቢሮን ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *