በኢትዮጵያ የሶስት ሚኒባስ ተሳፋሪ ያክል ቁጥር ያላቸው እናቶች በየቀኑ በወሊድ ምክንያት ይሞታሉ -ጤና ሚኒስቴር

66 ከመቶ የሚሞቱት የቅድመ ወለድ ክትትልና ምጥ ላይ ሆነው  ወደ ጤና ጣቢያ ወይም ሀስፒታል ዘግይተው ስለሚሄዱ  ነው።

ጤና ተቋማት ርቀት ፣ የመንገዶች ሁኔታ ፣  የትራንስፖርት ፣የፀጥታ ችግሮች  ፣ ጤና ተቋም ለመሄድ ዘግይቶ  መወሰን  ለነፍሰ ጡሮች  ጤና ጣቢያ ዘግይቶ መድረስ  እንደ ምክንያት ተገልፇል።

17,000 ጤና ኬላ እና  347  ሆስፒታሎች  ቢኖሩም 110 ሚልየን ህዝብ ላላት ኢትዮጵያ እነዚህ ተቋማት  በቂ አይደሉም ተብሏል።

ኢትዮጵያ  ከወሊድ  ጋር በተያያዘ የሚሞቱ እናትና ጨቅላ ህፃናት ቁጥር አሳሳቢ  የሆነባት ሀገር ሲሆን   እንደ ጤና ሚኒስቴር ገለፃ  ከሆነ  14,  000  ህፃናት በየአመቱ  ከወሊድ ጋር በተያየዘ በየአመቱ ሲሞቱ  38 እናቶች ደግሞ ወሊድ ላይ ይሞታሉ ተብሏል።

ጤናማ እናትነትን በኢትዮጵያ ለማስረፅ የታህሳስ ወርን በተለየ ሁኔታ ጤና ሚንስቴር ወሩን ለእናቶች ታሳቢ እንዲሆን አድርጓል። ለእናቶች እንዲሁም ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን እያጡ ላሉ ዜጎች “ርህራሄ እና አክብሮት ለእናትነት” በሚል ህይወትን ለመስጠት ህይወታቸውን እየከፈሉ ስላሉ እናቶች ሰፊ ስራዎችን እየሰራሁ ነው የሚለው መስሪያ ቤቱ በዘንድሮው መርህ “መከላከል በምንችላቸው ምክንያቶች የሚከሰቱ የእናቶችን ሞት በጋራ እንግታ/Let’s End Preventable Maternal Death Together!!” ሰፊ እቅዶችና እንቅስቃሴዎች ትግበራ ላይ ናቸው ተብሏል

ከዚህም ጋር በተያያዘ  የዓለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ 2017 ባወጣው ሪፖርቱ  የእናቶች ሞት ባደጉ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የሰራው ንፅፅራዊ አሃዝ ያለ ሲሆን፤ በማደግ ላይ ያሉ ድሃ ሀገራት 462/100,000 በህይወት ከተወለዱ ጨቅላ ህፃናት የሚሞቱ ሲሆን
በአንፃሩ ደግሞ ባደጉ ሀገራት 11/100,000 በህይወት ከተወለዱ ጨቅላ ሀፃናት ይሞታሉ

ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በመንግስታቱ ድርጅት የፀደቀው  በ2030 በአለም አቀፍ ደረጃ የእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ወደ 70/100,000 ዝቅ ለማድረግ እቅድ ይዞ ወደ እንቅስቃሴ ገብቷል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ከጠቅላላው ነፍሰ ጡሮች  48% ብቻ ሲሆኑ በእርግዝና ወቅት የሃኪም ክትትል የሚያደርጉ እናቶች ደግሞ ቁጥራቸው 74% ነው።

One thought on “በኢትዮጵያ የሶስት ሚኒባስ ተሳፋሪ ያክል ቁጥር ያላቸው እናቶች በየቀኑ በወሊድ ምክንያት ይሞታሉ -ጤና ሚኒስቴር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *