በኢትዮጰያ የመጀመሪያ የቴሌቪዥን ሴት ዜና አንባቢ የሆኑት ወይዘሮ እሊኔ መኩሪያ በ80 አመታቸው አረፉ

የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የድሮው  የአፍሪካ አንድነት ግንቦት 16 ቀን 1955 ዓ.ም በአዲስ አበባ መመስረቱ ጋር ተያይዞ አብሮ የተከፈተው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ የመጀመሪያ ሴት ዜና አንባቢ የነበሩት ወይዘሮ እሊኔ መኩሪያ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው ቤታቸው ሒወታቸው እንዳለፈ ፊደል ፖስት አረጋግጧል።

የሶስት ሴት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ እሌኒ በብስራተ ወንጌል ራዲዮ (በኋላ የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ድምጽ) ፣በወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማሕበር (ወሴክማ) የሰሩ ሲሆን እንዲሁም ፍራንሲስ ፋልሴቶ ላሳተማቸው “ኢትዮፒክ” አልበሞች ፕሮዲዊሰር ነበሩ።

በቢቢሲ አንግሊዘኛ የሰሩም ሲሆን በኢትዮጵያም ሬድዮ ” ሊስነርስ ቾይስ ” በተባለው የእንግሊዘኛ ዘፈን ፕሮግራም ላይ አዘጋጅ ሆነው ሰርተዋል።
በአሜሪካ ሀገር የነርስ ሙያ የተማሩ ሲሆን በሳንፎርድ ት/ቤት ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተምረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *