በአዲስ አበባ የሴት “የሒዩማን ሔየር “የቀን ኪራይ አምስት ሺ ብር ደርሷል

የገንዘብ ሚኒስተር የቤት አውቶሞቢልን ጨምሮ 38 አይነት የተለያዩ ሸቀጦች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ አገር እንዳይገቡ የባንክ መተማመኛ ሰነድ/LC እንዳይከፈትላቸው መወሰኑ ተከትሎ የሴቶች መዋቢያ ዕቃዎች ላይ በአዲስ አበባ ከ 50 አስከ 100 ፐርሰንት ጭማሪ መታየቱን ፊደል ፖስት መታዘብ ችሏል።

ከሰው ፀጉር ላይ ተወስዶ የሚሸጠው የሴት “የሒዩማን ሔየር ” የቀን ኪራይ ከ 2,000 ብር ወደ አምስት ሺ ብር አድጓል።
ከ 25 እስከ 30,000 ብር ድረስ ይሸጥ የነበረው ሴት “የሒዩማን ሔየር ” አብዛኞቹ መደብሮች ላይ ለመግዛት ” የለንም ” የሚል ምላሽ እየተሰጠ ነው።

በ 700 ብር የሚሸጡ ሰው ሰራሽ ዊጎች እሰከ 1,200 ብር እየተሸጡ ሲሆን 9 00 ብር የነበሩ የቅንድ መዋቢያዎች 2,000 ብር ሲጠሩም ተስተውሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *