የታከለ ኡማ አስተዳደር በአይነቱ ልዩ የሆነ የደሞዝ ጭማሪ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የመንግስት መምህራኖች በማድረግ በተወሰነ መልኩም ቢሆን የመምህራንን ወቅቱን ያገናዘበ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ለመመለስ ጥረት አድርጓል።
ፊደል ፓስት ባገኘው መረጃ መሰረት በሰርተክፌት ደረጃ ያሉ መምህራን ደሞዛቸው 1,828 ብር ወደ 3,943 ብር አድጓል። በዲግሪ ደረጃ ያሉ መመህራን ወርሀዊ ደሞዝ 3,137 ብር ወደ 6,193 ብር አድጓል ።በዲፕሎም ደረጃ ያሉ መምህራን ከ2,404 ወደ 4,609 ብር ሲያድግ የዋና ርዕሰ መምህራን ደሞዝ ደግሞ ከ8,236ብር ወደ 12,579 አድጓል።
ይሄ ያደገው ደሞዝ ተግባራዊ የሚሆነው በመጪው ሀምሌ 2012 ሲሆን እስከዛው ግን ሰርተክፌት ያላቸው መምህራን 3,328 ብር,፣ዲግሪ መምህራን 4,673 ብር ፣በዲፕሎም ደረጃ ያሉ መምህራን ደግሞ 3,904 ብር ደሞዝ እየተከፈላቸው ነው ።
በአዲስ አበባ የመንግስት ት/ቤቶች ከ20,000 በላይ መምህራን ይገኛሉ።
How about university lecturers????