ሐይማኖት በዳዳ ገሏል የተባለው ወጣት በከባድ ውንብድና ወንጀል ዛሬ ክስ ተመሰረተበት


የ28 አመቷን የጥቁር አንበሳ የድህረ ምረቃ የህክምና ተማሪ ሐይማኖት በዳዳን በስለት ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ/ም በኮሌጁ አስተዳደር ህንፃ ላይ በሚገኘው የላቦራቶሪ ቤተ ሙከራ ክፍል ለምርምር በገባችበት ወቅት ገሏል የተባለው ወጣት ደግነት ወርቁ በውንብድና ወንጀል አቃቢ ህግ ዛሬ ጷግሜ 5,2012 በልደታ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረተበት ሲሆን በመንግስት ጠበቃ የቆመለት ተከሳሽ ለመስከረም 11,2013,መልስ ይዞ እንዲቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቶታል ።
የተከሳሹ ጓደኛ ምህረቱ ሚጣ ተከሳሽ ወንጀሉን ሲፈፀም ተባባሪ ሆነሀል በሚል ክስ ቀርቦበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *