ለ40 ኮማ ውስጥ የነበረው የቀድሞ የፈረንሳይ እግር ኳስ ተጫዋች ጄን ፔሬሬ አዳምስ ማረፉ ተነገረ

በህክምና ስህተት ለ40 አመት በአልጋ ላይ ኮማ ውስጥ የነበረው የ73 አመቱ የቀድሞ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይና የፓሬሴን ዠርሜን ክለብ እግር ኳስ ተጫዋች ዛሬ ሒወቱ ማለፉን የፓሬሴን ዠርሜን በትዊተር ገፁ አሳውቋል።

22 ጊዜን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን መሰለፈ የቻለውና ” ጥቁር ጠባቂ ” ተብሎ ከሚጠራው ከማሪየስ ትሬሶር ጋር ከባድ አጋርነት ፈጥሮ የፈረንሳይ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ጋር አይረሴ ጊዜ ያሳለፈው ጄን ፔሬሬ አዳም ከ40 አመት የአንጎል ለመደበኛ የጉልበት ቀዶ ጥገና በስህተት የተሰጠው አንጎሎን ጎድቶት ለ40 አመት እራሱን ሳያውቅ በኮማ ውስጥ አንዲቆይ አድርጎታል።

አልጋ ላይ ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ሚስቱ በርናዴት በኒምስ ከተማ በሚገኘው ቤታቸው የንከባከበችው ሲሆን ከ14 አመት በፊት “ውሻ ሲጮህ ይሰማል ማሸተት እየቻለ ነው ግን ማየት አይችልም ” በማለት ተስፋ ሰጪ ነገር መናገሯ ይታወሳል።

አዳምስ እ.ኤ.አ በመጋቢት 1948 ሴኔጋል ዳካር ውስጥ ተወልዶ በሞንታርጊስ ከአያቱ ጋር በሐጂ ጉዞ የ 10 ዓመት ልጅ ሆኖ ወደ ፈረንሳይ መጣ ።

በፈረንሣይ አሳዳጊዎች አግኝቶ በሎሬት ውስጥ ለአከባቢ ክለቦች እግር ኳስ መጫወት የጀመረው በአንድ የጎማ ፋብሪካ ውስጥ ሲማር እና ሲሠራ ነበር።

በፈረንሳይም ለኒምስ እንዲሁም ለፒኤስጂ እ.ኤ.አ ከ1977-1973 ድረስ ተጫውቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *