ለ25 ቀናት የሚቆይ ” ክረምት እና ንባብ ” የተሰኘ የመጻህፍት አውደ ርዕይ ተከፈተ

ከገበያ የጠፉ መፅሀፍቶችንና አዳዲስ የሀገር ውስጥና የውጭ መፅሀፍትን የያዙ 15 የመፅሀፍት አካፋፋዮች እስከ 50% ቅናሽ በማድረግ ለአንባቢዎች መፅሀፍት የሚሸጡበት ለ25 ቀናት የሚቆይ ” ክረምት እና ንባብ ” የተሰኘ የመጻህፍት አውደ ርዕይ ዛሬ አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ኢክላስ ህንፃ ተከፍቷል። 11 አዲስ መፅሀፍትም ይመረቁበታል።

በዋልያ መፅሀፍት መደብርና በዋልያ ኢቨንትስ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ይኼ አውደ ርዕየይ ልጆችን መፅሀፍት አንዲያነቡ የሚያነሳሳ ፕሮግራም ሲኖረው እንዲሁም አባይ ግድብን እና ሌሎች ትልቅ የሀገሪቱን ታሪካዊ ፣ማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ ናኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ግጥሞች፣ ስነ ፅሁፎች እና ዲስኩሮች በደራሲዎች ፣በዩንቨርስቲ ምሁራንና ጋዜጠኞች ይቀርቡበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *