ሃሌ ሉያ ሆስፒታል በኢሳት ቲቪ በሐሰት ስሜ ጠፍቷል አለ

“ኢሳት ቴሌቭዥን የሆስፒታሉን ስም አጥፍቷል ።ጉዳዩን ፍርድ ቤት ወስጄዋለው ” ሃሌ ሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል

ሃሌ ሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮሮናቫይረስ ታካሚዎችን በሚልየን ብር ያስከፍላል ተብሎ በኢሳት ቴሌቭዥን የቀረበብኝ ዜና ሐሰተኛ ከመሆኑም ባሻገር በጎ ስሜን ለማጥፋት የቀረበ ነው አለ ።

ከ735 በላይ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎችን በተመጠጣኝ ዋጋ የህክምና ድጋፍ አድርጌ አንድ በርከት ያለ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውንእና በፅኑ ህሙማን ክፍል በማሽን እየታገዙ ሲተነፍሱ የነበሩ ሒወታቸው ያለፈ ታካሚን ያወጡትን ወጪ አይቶ ሃሌ ሉያ ሆስፒታል የኮሮናቫይረስ ታካሚዎችን በሚልየን ብር ያስከፍላል ተብሎ በኢሳት ቴሌቭዥን የቀረበብኝ ዜና ሐሰተኛ እና በጎ ስሜን ለማጥፋት የቀረበ ነው በማለት የሆስፒታሉ አስተዳደሮች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።

” ዜናው እኛ ላይ ተሰርቶ እኛ ሳንጠየቅ አንዴት ይሰራል ።ዜናው ሚዛናዊነት ይጎለዋል እንዳይተላለፍ ብለን በፍርድ ቤት ብናሳግድም ኢሳት ህግን ጥሶ አስተላልፏል ።ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደነዋል ” ሲሉ የሆስፒታሉ ባለቤት ፕ/ር ጌታቸው አደራዬ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *