የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ” ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች ካርታ ይፋ ማድረጊያ ቀንን ከመጋቢት 01 ቀን 2012 ወደ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ማዘዋወሩን አስታወቀ። “በሚለው የማህበራዊ ሚዲያ ዜናው የተጠቀመው ምስል በፎቶ ሾፕ የተቀነባበረ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከባለቤታቸው ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር ተነጣጥለው ተኝተው የሚያሳየውን ፎቶ የተጠቀመው ምስል በስህተት መሆኑን ለፊደል ፖስት አስታወቀ።
ዛሬ ቀን 5:50 አካባቢ የተለጠፈው ዜና ከአምሰት ደቂቃ በኋላ ከድርጅቱ ፌስ ቡክ ገፁ ተነስቷል።
በተቀነባበረው ፎቶ ላይ ቀዳማወዊ እመቤቷ አልጋ ላይ ተኝተው ጠ/ ሚኒስትሩ ደግሞ መሬት ፍራሽ ላይ ሆነው ይታያሉ።
ፊደል ፖስት ድርጊቱን ማን እንደፈፀመው ቢጠይቅም ድርጅቱ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል
ድርጅቱ ከለተፈጠረው ስህተትም ይቅርታ ጠይቋል።
ይፋዊ በሆነው የፌስቡክ ገፁ ላይ ይህንን ስህተት የፈጠሩ ጋዜጠኞቹን ከስራ ያገደ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በቀጣይ የሚወሰደውን እርምጃም እንደሚያሳውቅ ገልጿል።