በጥቁር ገበያው አንድ ዶላር አስከ 51 ብር ድረስ እየተገዛ ነው

በጥቁር ገበያው አንድ ዶላር አስከ 51 የ ብር ድረስ እየተገዛ ሲሆን ከባንክ መግዣ ጋር በአንድ በዶላር እሰከ 12.60 ብር ልዩነት እያሳየ ነው።

ፊደል ፖሰት በደረሰው መረጃ መሰረት በአንድ ወር ልዩነት ውስጥ በጥቁር ገበያው የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ ከሶስት ብር በላይ ከፍ ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጥቁር ገበያው አንድ ዶላር አስከ 51 ብር እየተገዛ ነው ።

ባንኮች አንድ ዶላርን በ38.60 እየገዙ ሲሆን በጥቁር ገበያውና በባንኮች የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ አስከ 12.60 ብር ድረስ ልዩነት እያሳየ ነው።
በኢትዮጵያ የገንዘብ ኖት ከተቀየረ በኋላ የዶላር ዋጋ እያሻቀበ የመጣ ሲሆን ከውጭ በሚመጡ እቃዎች ላይ ባለፉት አራት ውስጥ እስከ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ነው።

ለዶላር ዋጋ መጨመሩ በውል የተጠና ጥናት ባይኖርም ወደ በሀገሩቱ የነበረው ጦርነት ፣ኮሮናቫይረስ የሀገሪቱን የንግድ አንቅሳቃሴ በመጉዳት የዶላር አቅርቦትን የቀነሰ ሲሆን ከብር ኖቱ መቀየር ጋር ተያይዞ በህገወጥ መንገዱ ዶላርን ከገበያ ስብስቦ ሀብትን ወደ ዶላር የመቀየር ሁነቶች ለዶላር ዋጋ መጨመር እንደ መላ ምት በአንዳንድ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይቀመጣሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *